በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ አዲስ አዳጊውን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያስተናገደው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የ3-1 አስደንጋጭ ሽንፈት ደርሶበታል።
ለወልዋሎ አ.ዩ. ፕሪንስ ሶቨርን 16ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ በማድረግ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል። በሁለተኛው አጋማሽ በ1 ደቂቃ ልዩነት 60 እና 61ኛው ደቂቃ ላይ በረከት ተሰማ እና አፈወርቅ ሀይሉ ያስቆጠሯቸው ግቦች ወልዋሎ አ.ዩ. አሸናፊ ማድረግ ችለዋል። አልሀሰን ካሉሻ 88ኛው ደቂቃ ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ ግብ ማስቆጠር ቢችልም ቡድኑን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም።
በሌላ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከተማ እና ወልድያ ከተማ ተገናኝተው ያለምንም ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። 94ኛው ደቂቃ ላይ የወልዲያ ከተማ ተከላካዮች ኳስ በእጅ በመንካታቸው የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት አብዱራህማን ሙባረክ (ግሪዳው) ሳይጠቀምበት በመቅረቱ ፋሲል ከተማ ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።