*…. ለቦታው ሰባት አሰልጠሰኞች ተፎካክረዋል….
በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ የሚነገር ታሪክ ቢኖረውም በቅርብ አመታት ግን እያሽቆለቆለ የመጣው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የቀድሞ የስሁል ሽረ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በይፈ ቀጥሯል።
ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የገላኑን ዳዊት ታደለን ለመቅጠር ከጫፍ ደረሰ እየተባለ በሚወራበት በአሁኑ ወቅት አምና ድሬዳዋ ከተማን ይዞ የነበረውን አሰልጣኝ ሳምሲን አየለን መቅጠራቸው ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል። አመራሮቹ ከአሰልጣኝ ዳዊት ጋር በበርካታ ጉዳዮች ተስማምተው ሀሳባቸውን ያስቀየረው ጉዳይ አልታወቀም።
- ማሰታውቂያ -
በኢትዮጵያ እግር ኳስ የማይረሳ ታሪክ የሰራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመጣበት አመት ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ አነጋጋሪም ሆኗል። ክለቡ በተለይ እግርኳስ ወዳዱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ደንድርን ካጣ ወዲህ ማንጸባረቅ አለመቻሉና ለማደግ ከፍተኛ ትግል ወደ ሚጠይቀው ከፍተኛ ሊግ መውረዱ በርካታ የስፖርት ቤተሰብን አስቆጭቷል።
በ2016 ኢትዮ ኤሌክትሪክን መረከቡን ያረጋገጠው አሰልጣኝ ሳምሶን ከክለቡ ስራ አስኪያጁ አቲ ሲሳይ ጋርም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከፋሲል ከነማ ጋር እያደረገ ያለውን ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ተገኝተው እየተከታተሉ ይገኛሉ።
አቶ ሲሳይ ለማ ከአዳማ ለሀትሪክ ድረገጽ እንደተናገሩት “አሰልጣኝ ሳምሶንን ለ2016 በሱፐር ሊጉ ለሚካፈለው ቡድናችን ቀጥረነዋል በቀጣይ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ወደነበረበት ክብር ለመመለስ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ ተስፋ እናደርጋለን ከሱ ጋር ፕሪሚየር ሬሊግና ከፍተኛ ሊግ ለይ እየሰሩ ያሉ 7 አሰልጣኞችን አነጋግረን በመመዘኛ አራት ቀርተው ከአራቱ ደግሞ አቶ ሳምሶንን መርጠን ውላችንን ፈጽመናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ ሰባት አልጣኞች መወዳደራቸውን ገልጸው ስማቸውን ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል።