የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተያያዘ ጠንካራ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደተናገሩት “ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተያያዘ ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው እንዴት ልንጠቀምባቸው እንችላለን በሚለው ዙሪያም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር እየመከርን ነው ፊፋ የሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ጉዳይን እንዴት እንደፈታም እያየነው ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።
ዋና ስራ አስፈጸሚው ሲናገሩ “ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተያያዘ ብሄራዊ ቡድናችንን እንዴት መጥቀም ይችላሉ ከሀገራችንና ከፊፋ ህግ አንጻርስ ጉዳዩ እንዴት ይፈታል የሚለውን እየመረመርን ነው በተለይ የፌዴሬሽናችን ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሳሙኤል የሺዋስ ለሌላ ስራ ፈረንሳይና ስዊዘርላንድ በሄዱበት ወቅት ሁለቱ ሀገራት በሚገኙ የፊፋ ቢሮዎች በመገኘት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አመራሮች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ አውርተዋል በዚህ አጋጣሚ ዶክተር ሳሙኤልን በፌዴሬሽናችን ስም ማመስገን እፈልጋለሁ” በማለት ተነግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
” ከትውልደ ኢትዮዽያዊያን ጋር በተያያዘ በቀጣይ ለሚዲያው የምናዘጋጀው መድረክ ይኖራል ያኔ ሰፋ አድርገን እንመክራለን ሌሎች ሀገራትም ያገኙትን እድል እንደምናገኝ ርግጠኞች ነን” ያሉት አቶ ባህሩ ” ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተያያዘ በቀጣይ ትልቅ የምስራች ይዘን እንመጣለን” ሲሉ ያለውን ተስፋ አስረድተዋል።