በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ለረዥም ግዜያት ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ርቀዉ የሚገኙት የትግራይ ክለቦች ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም እና ድጋፍ ለማድረግ የታለመለት ጉዞ በዛሬው እለት ወደ መቀሌ ከተማ ተደርጓል።
ወደ መቀሌ ከተማ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚንስትር አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች የተጓዙ ሲሆን በመቀሌ ቆይታቸዉም ስለትግራይ ክለቦች ቀጣይ ሁኔታ የሚመክሩ ይሆናል።