የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአሜሪካ ለወዳጅነት ጨዋታ አምርቶ ባደረጋቸዉ ጨዋታዎች በአሜሪካ ክለቦች መልማዮች እይታ ዉስጥ የገቡ ተጫዋቾችን ዝርዝር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን አስታዉቋል።
በዚህም መሰረት ሽመልስ በቀለ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ ቢኒያም በላይ ፣ አቤል ያለው ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ረመዳን የሱፍ እና ማርከስ ቬላዶ-ፀጋዬ በልዩ ሁኔታ በመልማዮች እይታ ዉስጥ ገብተዉ ምልከታ ሲደረግባቸዉ እንደነበር ገልፀዋል።
ከተጠቀሱት ተጫዋቾች ውስጥ ጋቶች ፓኖም እና አቤል ያለው ከዲሲ ዩናይትድ በተጨማሪ በሌላ አንድ ክለብ መልማዮች ተፈልገው እንደነበር ገልፀው አቤል በክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ውል ስላለው ጥያቄው ወደ ክለቡ እንዲሄድ አድርገን ውል የሌለው ጋቶች ፓኖም እዛው ቀርቶ ዕድሉን እንዲሞክር አድርገናል ብለዋል።