በመሸሻ ወልዴ
የተወለደው፡- አዲስ አበባ ፍልውሃ
አካባቢ
አሁን የሚኖረው፡- ሲዊዘርላንድ ዙሪክ
የተጫወተባቸው ክለቦች፡- ለመድን ከታዳጊ አንስቶ
እስከዋናው፣ ለኤሌክትሪክ፣ ለትራንስ ኢትዮጵያ፣
ለአዳማ ከተማ እና ለሐዋሳ ከተማ
አሁን የሚጫወትበት ክለብ፡- ለስዊዘርላንዱ
ኤፍ.ሲ ሱርቢጃ ዙሪክ
ያገኛቸው ክብሮች፡- ከመድን ጋር ሁለት ጊዜ የጥሎ
ማለፍ ዋንጫ፣ እንደዚሁም ከስዊዘርላንዱ ኤፍ.ሲ
ሱርቢጃ ቡድን ጋር የ3ኛ ዲቪዚዮን ሻምፒዮና
በመሆን ክለቡን ወደ 2ኛ ዲቪዚዮን ያሻጋገሩበት
ዋንጫ፣ በግል ደግሞ በአውሮፓ በሚካሄደው
የኢትዮጵያኖች የኮሚኒቲ ቶርማንት ውድድር ላይ
ከኢትዮ- ስዊዝ ቡድን ጋር ሻምፒዮን ከመሆን
አልፎ የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች እና ኮከብ ግብ
አግቢ በመባል ሽልማትን አግኝቷል፡፡
የምንጊዜም ምርጡና ጀግናው ተጨዋች:- “ለእኔ
ዮርዳኖስ አባይ /ቡሎ/ ነው፤ ዮርዳኖስ ኳስን
በፈለግከው መንገድ አቅልሎ ሊጫወትልህ የሚችል
እና ጎል አዳኝም ተጨዋች ስለሆነ እሱን ቀዳሚ
ምርጫዬ አድርጌዋለሁ”፡፡
ከአጠገቡ አብሮት ሲጫወት እርካታ የሚሰጠው
ተጨዋች:- “ዮሴፍ ተስፋዬ /ቫንባስተን/ ነዋ! እሱ
ልዩ ችሎታ ያለው ተጨዋች ነው፤ ከአጠገቤ ሆኖ
ሲጫወትም የመጀመሪያዬ ተመራጬ ያደረግኩት
ኳሱን ስይዝ ሁሌም እንዳልቸገር ሊቀበልኝ ዝግጁ
የሆነ ተጨዋች በመሆኑ ነው፤ በዛ ላይ የምርጥ
ስብዕናም ባለቤት ነው”፡፡
ከጎኑ አብሮት ባለመጫወቱ የሚቆጨው ተጨዋች:-
“በእዚህ የማስቀድማቸው ተጨዋቾች ወንድሜ
ተክሌ ብርሃኔን /ገመዳ/ እና ዮርዳኖስ አብይን /
ቡሎ/ ነው፤ ከእነሱ ጋር አለመጫወቴ ሁሌም
ይቆጨኛል”፡፡
ከእግር ኳስ ተጨዋቾች ውስጥ በቀልደኝነቱ
ያዝናናው ስለነበረው ተጨዋች:- “ብሩክ እስጢፋኖስ
/ካንቶና/ ነዋ! ብሩክ የእውነት ቀልድ ይችላል፤
መድን በነበርንበት ሰዓት በፉገራው በጣም
ያዝናናኝና በሳቅም ያንፈራፍረኝ ነበር”፡፡
ከእግር ኳስ ውጪ አብሮት ሲውል በጣም ደስ ይለው
ስለነበረው ተጨዋች:-“የመጀመሪያው ተመራጬ
የቀድሞው እግር ኳስ ተጨዋችና ጓደኛዬ የነበረው
ደምስ ኑሪ ነው፤ ከዛ ውጪ የሰፈር ጓደኞቼ
እንዳሉ ሆነው ከሚካኤል ጆርጅም ጋር አብረን
ስንውል በጣም ነበር ጥሩ ስሜት የሚሰማኝ”፡፡
ከእግር ኳስ ውጪ ለመዋያ የሚመርጠው ቦታ:-
“ቤተክርስቲያንን ነው የማስቀድመው፤ ከዛ ውጪ
ከወላጅ እናቴ ጋር ስውል በጣም ደስ ይለኛል”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነቱ ያላሳካቸው ነገሮች:-
“የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለአንድም ጊዜ ቢሆን
አንስቼ የማላውቅ ተጨዋች መሆኔ ነውና ይሄ
የቁጭት ስሜትን ይፈጥርብኛል”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነቱ የሚመርጠው የማሊያ
ቁጥር እና ምክንያቱ:- “9 ቁጥር የመጀመሪያ
ምርጫዬ ነው፤ ይሄን የማሊያ ቁጥር አጥልቄ /
ለብሼ/ ልጫወት የቻልኩትም ከልጅነቴ ዕድሜ
ጀምሮ ታላቅ ወንድሜ ተክሌ ብርሃኔ ለብሶት
ሲጫወት እያየሁት ስላደግኩና ከዛም ውጪ
የብራዚላዊው ትልቁ ሮናልዶ አድናቂም ስለሆነኩ
ነው”፡፡
ለጨዋታ ወደ ሜዳ ከመግባቱ በፊት በመልበሻ
ክፍል ውስጥ ስላለው ልምድ:- “የእግር ኳስን
ከመጫወታችን በፊት ሁሌም ለብቻዬ ሆኜ ፀሎቴን
ለፈጣሪዬ አደርሳለሁ”፡፡
የእግር ኳስን በተቃራኒነት ሲገጥሙ በጣም
ደስ ይለው የነበረ ክለብ:- “ኢትዮጵያ ቡና ነዋ!
የደጋፊዎቹ ህብረ-ዝማሬ በጣም ደስ ስለሚልና
ስታዲየሙ ደግሞ ሁሌም ስለሚሞላ ከእነሱ ጋር
ስንጫወት የተለየ የደስታ ስሜት ይሰማኛል”፡፡
በመሀል ባልገባ አጨዋወት የምታደንቀው
ተጨዋች:- “ብዙ ናቸው፤ ያም ሆኖ ግን በተለየ
መልኩ በእዚህ አጨዋወት የተካኑ ናቸው ብዬ
ከፍተኛ አድናቆት የምሰጣቸው ተጨዋቾች ካሳዬ
አራጌ፣ አፈወርቅ ኪሮስ፣ ያሬድ ዝናቡና መስዑድ
መሐመድ ናቸው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ስላስቆጠረው
ምርጥ ግብና ግቧን ካገባ በኋላ ስለዳረገው የተለየ
ድርጊት:- “ምርጧ ግቤ ኢትዮጵያ መድን እያለሁ
በቡና ላይ ከሩቅ መትቼ ያስቆጠርኳት የማሸነፊያ
ጎል ናት፤ ያኔ ግቧን ባለቀ ሰዓት ካገባው በኋላም
ከማሊያዬ ስር ለብሼው የነበረውን የገብርኤል
ምስል ነበር ለተመልካቾች ያሳየሁት”፡፡
ከተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾች ኳስን ከእግሩ ስር
ለመንጠቅ አስቸጋሪ ስለሆነበት ተጨዋች:- “በዚህ
ወንድሜን ተክሌ ብርሃኔን አስቀድማለሁ፤ ከእሱ
ጋር ሁሌም ተቃራኒ ሆኜ ስጫወት ኳስ ልነጥቀ
ይቸግረኝና ይከብደኝም ነበር”፡፡
በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ በጣም የሚወደው
ምግብ:- “ኢትዮጵያ የነበርኩ ሰዓት እንጀራ
ፍርፍርን ሲሆን ወደ ስዊዘርላንድ ከመጣሁበት
ሰዓት ጀምሮ ደግሞ ለእኔ የተመቸኝ ምግብ
“ካክሌት” የሚባል ምግብ ነው፤ “ካክሌት” በድንችና
በቺዝ የሚበላ ተወዳጅ ምግብ ነው”፡፡
በምን እናጠቃል:- “በምስጋና፤ በመጀመሪያ
እንደ ቀድሞ የእግር ኳስ ተጨዋችነቴ እኔን
አፈላልጋችሁና አስታውሳችሁ የአዲሱ አምዳችሁ
እንግዳ ስላደረጋችሁኝ ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ፤
ከዛ በመቀጠል ደግሞ ሁሌም የኳስ አሰልጣኞቼን
እና ትልቅ ወንድሜን ተክሌ ብርሃኔን እንደዚሁም
ደግሞ ከሰባት አመት በፊት ወደ ስዊዘርላንድ
ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮ-ስዊዝ የሚባል እነ
ሰይፉ ውብሸት /ፕሮም/ እና ፈለቀ ሞሼን የያዘው
የቀድሞ ተጨዋቾች የተሰባሰቡበት ቡድን አለና ለእ
ኔ እንደ ቤተሰብ ያህል የምመለከተው የእነዚህን ቡ
ድን አጠቃላይ አባላቶችን ማመስገን እፈልጋለሁ”፡፡