በክረምቱ የዝውውር መስኮት እምብዛም ስማቸው ካልተነሱት ክለቦች መካከል የነበረው ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ፈራሚውን ይፋ አድርጓል ።
በሰርቢያው አሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪች የሚመራው ቡድኑ ግብ ጠባቂውን አስራት ሚሻሞን ከአዲስ አዳጊው ሀምበሪቾ ዱራሜ አስፈርሟል ።
አስራት ሚሻሞ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሀምበሪቾ ዱራሜ ከማሳለፉ በፊት በወላይታ ድቻ እና ሀድያ ሆሳዕና ተመሳሳይ ሁለት ሁለት ዓመታትን አሳልፏል ።
ግብ ጠባቂው ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የቡናማዎቹን መለያ ለብሶ ለመጫወትም ፊርማውን አኑሯል ።
- ማሰታውቂያ -
ቡናማዎቹ አስቀድመው ከግብ ጠባቂው ህዝቄል ሞራኬ ፣ ሔኖክ ድልቢ እና ኩዋኩ ዱሃ ጋር መለያየታቸው ይታወሳል ።