በአሰልጣኝ ዩሀንስ ሳህሌ እየተመሩ በዝዉዉር መስኮቱ ላይ በንቃት በመሳተፍ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ እንዲሁም የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት ነብሮቹ ሶስት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ ሲቀላቅሉ የአንድ ተጫዋቻቸዉን ዉል አድሰዋል።
ሀዲያ ሆሳዕናዎች የቀድሞዉን የሲዳማ ቡናን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የነበረዉን ቴዎድሮስ ታፈሰን በሁለት ዓመት ኮንትራት ወደ ስብስባቸዉ ሲቀላቅሉት እንዲሁም የቀድሞዉን የአዳማ ከተማዉን አጥቂ ዳዋ ሁቴሳን እና የባህርዳር ግብ ጠባቂ የነበረዉን ታፔ ኤልዛየርንም በይፋ በሁለት አመት ኮንትራት ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
እንዲሁም ነብሮቹ የመስመር አጥቂያቸዉን የሰመረ ሀፍታይን ዉል ለተጨማሪ ሁለት አመታት አድሰዋል።