ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት በነገው ማክሰኞ ጥቅምት 14/2010 ዓ.ም ዕትሟ እንደተለመደው ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ ትኩስና አዳዲስ መረጃዎቿ ጋር በእጅዎ ለመግባት ዝግጅቷን አጠናቅቃለች፡፡ ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
– ከሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንትነት እና ስራ አስፈፃሚ አባልነት በዕጩነት የቀረቡትን ሰዎች እስካሁን ይፋ ባያደርግም ሀትሪክ ግን ታማኝ ምንጮቿን ተጠቅማ በዚህና በዕጩዎቹ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎችን ይዛለች፤ ለመሆኑ ቀጣዮቹ የፌዴሬሽኑ እነማን ይሆኑ?
– በሲቲ ካፑ ፍፃሜ የነበረውን ድባብና የተፈጠረውን ረብሻ ተከትሎ ከሁለቱም ክለቦች (ከቅ/ጊዮርጊስ ሙሉአለም መስፍን /ዴኮ/ እና ከኢት.ቡና እያሱ ታምሩ) የሚሉት ይኖራል፡፡
– “Oldies but Goodies” በተሰኘውና የቀድሞ ተጨዋቾቻችን በሚቀርቡበት አምድ ላይ የዚህ ሳምንት እንግዳችን የሆነው የቀድሞው የመብራት ሀይል እና የብ/ቡድናችን ምርጥ ተጨዋች የነበረው ሃይሉ አድማሱ (ቻይና) ነው፡፡ ወደ ኋላ በትዝታ ወስዶን የተጨዋችነት ወርቃማ ዘመኑን ያስቃኘናል፡፡ በጣም ይወዱታል፡፡
- ማሰታውቂያ -
– የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤውን ወደ አፋር ሰመራ ከወሰደው በኋላ መልሶ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ አምጥቶታል፤ መጀመሪያ ለምን ወደዛ ወሰደው አሁንስ ለምን መለሰው? በዚህም ዙሪያ ያልተሰሙ ነገሮችን ይዘናል፡፡
– ቅዳሜና እሁድ በተካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተፈጠሩ የተባሉት ውዝግቦች ምን ይመስላሉ? በስፋት ዳስሰነዋል፡፡
– ከባህር ማዶም የሳምንቱን መጨረሻ ጨዋታዎችና ሌሎችንም በርካታ መረጃዎችን ይዘናል፤ እንደሚወዷቸው ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ባሉበት ቦታ ሆነው ትኩስና አዳዲስ የሀገር ውስጥ መረጃዎችን ሲፈልጉ ደግሞ ድረ-ገፃችንን www.hatricksport.com መጎብኘት ይችላሉ፡፡ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 14/2010 ዓ.ም ለንባብ የምትበቃው ሀትሪክ ስፖርት የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፤ መልካም ንባብ!