ከቀናት በፊት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊመጡ ከስምምነት የተደረሰባቸዉ ሁለት የዉጪ ሀገር ተጫዋቾች በዛሬው እለት በዪፋ ክለቡን ተቀላቅለዋል።
በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ ለቀጣዩ የዉድድር አመት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከቀናት በፊት ወደ ክለቡ ሊያመጧቸዉ በቃል ደረጃ የተስማሟቸዉን ተጫዋቾች በይፋ ወደ ክለቡ ቀላቅለዋል።
ከቀናት በፊት ከክለቡ ጋር በቃል ደረጃ ስምምነት የፈጠሩት ናይጄሪያዊዉ ሞሰስ ኦዶ ቶቹኩ እና ጋናዊዉ ክዋሜ ኦዶም ፍሪምፖንግ በትላንትናዉ እለት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን በዛሬው እለት ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት በማምራት በይፋ የሁለት ሁለት አመት ኮንትራት ለቅዱስ ጊዮርጊስ አኑረዋል።