ከቀናት በኋላ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታ ከዛንዚባሩ ክለብ KMKM ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው እና በዝውውር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ በመቀላቀል ላይ የሚገኘዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአማካዩ እና አምበሉ ሀይደር ሸረፋ ጋር መለያየቱ ዕርግጥ ሆኖአል።
በዚህም ከዚህ ቀደም ለደደቢት ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ጅማ አባጅፋር እና መቀለ 70 እንደርታ መጫወት የቻለዉ እና ያለፉትን አራት ያህል አመታት ደግሞ በፈረሰኞቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሀይደር ሸረፋ ከአመታት በኋላ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ተጫዋቹ ምሽቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።