በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ 9 አዳዲስ ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ስሑል ሽረዎች ከብሩክ ተሾመና ዲሜጥሮስ ወልደስላሴ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት አጋማሽ ስሁል ሽረን በመቀላቀል ቡድኑ ከወራጅነት እንዲተርፍ ያገዘው ሁለገብ ተጨዋቹ ብሩክ ተሾመ ከግማሽ ውድድር ዓመት ቆይታ በኃላ በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይትዋል።የቀድሞው የጅማ አባጅፋር፣ደደቢት፣ተጨዋች ብሩክ በግማሽ ዓመት የስሁል ሽረ ቆይታው የቀኝ መስመር ተከላካይ፣የመሀል ሜዳ አማካይ ና የመሀል ተከላካይ ሆኖ መጫወት ችሏል።ሌላኛው ከስሁል ሽረ ጋር የተለያየው ተጨዋች ዲሜጥሮስ ወልደስላሴ ነው፤በ2011 ከአዲስ አበባ ከተማ የፈረመው ዲሜጥሮስ በአንድ ዓመት ቆይታው ስሁል ሽረን በአምበልነት መርቷል።የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ፣ሀረር ቢራና አዳማ ከተማ ተከላካይ ዲሜጥሮስ በክረምቱ ከስሁል ሽረ ጋር የተለያየ 10ኛው ተጨዋች ሆኗል።
በተያያዘ ዜና ትላንትና የሥስት ነባር ተጨዋቾቹ ውል ያራዘመው ስሁል ሽረ ከሥስቱ ተጨዋቾች በተጨማሪ የነፃነት ገብረመድህን፣ጌታቸው ተስፋይ፣ክብሮም ብርሃነ፣ዋልታ ዓንደይ፣ተኽላይ በርሀን ውል ሲያራዝም በቀጣይ ቀናትም 4 ተጨዋቾችን ከሁለተኛ ቡድኑ ሚያሳድግ ይሆናል።