ከቀናት በፊት የሪችሞንድ ኦዶንግ ዝውውርን ያጠናቀቁት ብርቱካናማዎቹ ከድሬዳዋ ፖሊስ ሥስት ተጨዋቾቹን ማስፈረሙን በይፋዊ የክለቡ ፌስቡክ አድራሻ ገልፀዋል።
ላለፋት ቀናት ከቡድኑ ጋር ቢሾፍቱ ላይ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩት ሳሙኤል ዘሪሁን፣ፈርሃን ሰይድና ከድር ደበበ ከድሬዳዋ ጋር ሚያቆያቸውን ውል በይፋ ተፈራርመዋል።
ከድሬዳዋ ጋር በተያያዘ ዜና አዲስ የተመሰረተው የሊግ ካምፓኒ አቢይ ኮሚቴ የስታድየሞች ግምገማውን በድሬዳዋ ስታድየም ጀምርዋል።ባሳለፍነው አመት የመጫወቻ ሜዳ እድሳት፣የመሮጫ ትራክ ንጣፍ እና የመቀመጫ ወንበሮች ገጣማ የተሰራለት ይህ ስታድየም በአብይ ኮሚቴው በተቋቋመው ንኡስ ኮሚቴ አማካኝነት የተጎበኘ ሲሆን የሜዳው አጥር እና ከእድሳቱ ጋር ተያይዞ በሜዳው ዙርያ ሚገኙ ተረፈ ቁሳቁሶች ፕሪምየር ሊጉ ሳይጀመር እንዲነሱ አሳስበዋል።