በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እየተመሩ በተጠናቀቀዉ አመት ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ የቻሉት እና በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻሉት ኢትዮ ኤሌትሪኮች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋል።
የመጀመሪያው ፈራሚ ያለፉትን አመታት በኢትዮጵያ ቡና ቤት ማሳለፍ የቻለዉ የግራ መስመር ተጫዋቹ ሚኪያስ መኮነን ሲሆን ሁለተኛ ፈራሚ በመሆን ክለቡን የተቀላቀለዉ ደግሞ የቡድን አጋሩ አልአዛር ሽመልስ ሆኗል። እንደ ሚኪያስ ሁሉ ያለፈዉን አመት በቡናማዎቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ እና ከዚህ ቀደም ለአዲስ አበባ ከተማ መጫወት የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ አላዛር ሽመልስ በአንድ አመት የስምምነት ዉል ወደ ኢትዮ ኤሌትሪክ ማምራቱ ተረጋግጧል።