የኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን የፊፋ የቴክኒክ ኤክስፐርት መሆን ተከትሎ ከአሰልጣኛቸዉ ጋር በይፋ የተለያዩት ባህርዳር ከተማዎች አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም አዉስኮድን ፣ አማራ ዉሀ ስራን ፣ ወልቂጤ ከተማን እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ማሰልጠን የቻለዉ ደግአረግ ይግዛው የትዉልድ ከተማዉን ክለብ ባህርዳር ከተማ ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማውን ማኖሩ ተረጋግጧል።