By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጨዋታ ዘገባ | አዞዎቹ የዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን አጣጥመዋል
Share
Notification Show More
Latest News
በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ
ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች መቐለ 70 እንደርታ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
መቻልዜናዎችአርባምንጭ ከተማየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | አዞዎቹ የዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን አጣጥመዋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 3 years ago
Share
SHARE

በሊጉ የሶስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ መቻልን በመርታት የውድድር ዓመቱ ቀዳሚ ሶስት ነጥቡን አግኝቷል ።

መቻል በሁለተኛው ሳምንት በአዳማ ከተማ በተረቱበት ጨዋታ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ
ሶስት ለውጦችን ያደረጉ ሲሆን በቶማስ ስምረቱ ፤ በሀይሉ ግርማ እና ተሾመ በላቸው ምትክ አሚን ነስሩ ፤ ተስፋዬ በላቸውን እና ሳሙኤል ሳሊሶን ያሰለፉ ሲሆን በአርባምንጭ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ በኢትዮጵያ መድኅን በአስገራሚ ሁኔታ ከተሸነፉበት ጨዋታ አምሰት ለውጦችን በማድረግ አቤል ማሞ ፤ በርናንድ ኦቼንጌ ፤ ወርቅይታደስ አበበ ፤ አሸናፊ ፊዳ እና አሸናፊ ኤልያስን በማሰለፍ ይስሀቅ ተገኝ፤ እዮብ በቀታ ፤ ሙና በቀለ ፤ ተመስገን ተስፋዬ እና አህመድ ሁሴንን በተጠባባቂ ወንበር ላይ አስቀምጠው ጨዋታውን ጀምረዋል ።

በጨዋታው መቻሎች ኳስን ከኋላ መስርተው በመውጣት ወደ አርባምንጭ ከተማ የግብ ክልል የመድረስ አላማን ይዘው የገቡ ቢመስሉም በተደራጀ የመከላከል አንቅስቃሴ ጨዋታውን ያደረጉት አዞዎቹ ይህን በቀላሉ ከማድረግ አግደዋቸዋል ።

- ማሰታውቂያ -

መቻሎች ምንም እንኳን በተለይም በመሀል የሜዳው ክፍል ላይ እንደፈለጉት ለመንቀሳቀስ የተቸገሩ ቢሆንም በመስመሮች በኩል የአዞዎቹን የኋላ ክፍል ሰብረው ለመግባት ጥረቶችን አድርገዋል ።

በጨዋታው 24ኛው ደቂቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መቻል የግብ ክልል የደረሱት አርባምንጭ ከተማዎች መሪ የሆኑበትን ግብ አስቆጥረዋል ። ቡታቃ ሸመና ባልተጠበቀ ሁኔታ በሳጥን ውሰጥ የላከለትን ኳስ አሸናፊ ኤልያስ ከመረብ አሳርፎታል ።

የአርባ ምንጭ ከተማ መሪነት ከስደስት ደቂቃዎች የዘለቀ አልነበረም ። በ29ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር የተሻገረውን ኳስ በርናርድ ኦቼንጌ በእጁ በመንካቱ የተሰጠዉን የፍፁም ቅጣት ምት ምንይሉ ወንደሙ አስቆጥሮታል ።

 

በ37ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳሊሶ ከቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ የመታው ኳስ በአቤል ማሞ ተመለሰ እንጂ መቻልን መሪ ሊያደርግ የሚችል ነበር ።

በተለይም ከኳስ ውጪ ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የነበሩት አርባምንጭ ከተማዎች የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ አንድ ደቂቃ ቀደም ብሎ ሁለተኛ ግብ አስቆጥረዋል ። የመጀመሪያው ግብ ሲቆጠር አመቻችቶ ያቀበለው ቡታቃ ሸመና በግሩም ሁኔታ ወደ ግብ ክልል ያሻገረውን ኳስ ተመስገን ደረሰ በተክለማርያም ሻንቆ መረብ ላይ አሳርፏል ።

በሁለተኛው አጋማሽ መቻሎች ዳግም ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን የአርባምንጭ ከተማ ሳጥን ውሰጥ መግባት ግን አዳጋች ሆኖባቸው ነበር ። በዚህም ኳሶችን ከርቀት ለመሞከር የተገደዱ ሲሆን በተስፋዬ አለባቸው ፤ ፍፁም አለሙ እና ከነአን ማርክነህ አማካኝነት ያደረጓቸው የግብ ሙከራዎች ውጤታማ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል ።

በአርባምንጭ ከተማ በኩል ይዘው የገቡትን የጨዋታ እቅድ በተገቢ ሁኔታ መተግበር የቻሉ ሲሆን በተወሰኑ አጋጣሚዎች በመልሶ ማጥቃት ዕድሎችን ለመፍጠር ችለው ነበር ።

በተለይም በ64ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ሱራፌል ዳንኤል ከግራ መስር አቅጣጫ ያሻገረውን ኳስ ወርቅይታደስ አበበ አግኝቶ ሳይጠቀምበት የቀረው ኳስ ለአዞዎቹ አስቆጪ ነበር ።

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይ በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት መቻሎች ግብ ለማግኘት ያደረጓቸው ጥረቶች ሳይሳኩ ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ የ2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

በአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ጥቅምት 9 (ረቡዕ) 7:00 ላይ አርባምንጭ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን የሚገጥም ሲሆን ጥቅምት 11 (አርብ) በተመሳሳይ ሰዓት መቻል ከፋሲል ከነማ ይጫወታል ።

You Might Also Like

በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት 48 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበላቸው
Next Article የጨዋታ ዘገባ |ወላይታ ድቻ እና ኢትዮ ኤሌትሪክ ጨዋታቸዉን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንዜናዎችሲዳማ ቡና

ዓለም-አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት የሲዳማ ቡና ይግባኝ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ውሳኔ ሰጥቷል።

Fitsum Nigusse By Fitsum Nigusse 7 months ago
ፋሲል ከተማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን አስፈርሟል
​የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ውጤቶችና የደረጃ ሰንጠረዥ 
በመከራ ተፈትና የተረፈችው የተስፋሁን ጋዲሳ ህይወት
ወልቂጤ ከተማ አመቱን በድል ሲደመድም ፤ መዉረዳቸዉን ያረጋገጡት ሻሸመኔዎችም ሀምበሪቾን በማሸነፍ የሊጉን ቆይታቸዉን አገባደዋል !!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?