*…ሊዲያ ታፈሰ…
*…ኢንተ.አርቢትር…
*… የቅርጫት ኳስ ስፖርተኛ…
*..ወንዶችን በቻን ውድድር በማጫወት የመጀመሪያ ሴት ዳኛ
*…የሴቶች የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜን ያጫወተች…
*…የአፍሪካና የአለም ዋንጫዎችን በተደጋጋሚ ያጫወተች ….
….. ወዘተ….
…….ከ1992-2015…..
ክንዴ ሙሴ በሲዳማ ደርቢ…..
ሊዲያ ታፈሰ በአዲስ አበባ ደርቢ…
- ማሰታውቂያ -
ኢትዮጵያን ከብሄራዊ ቡድኖቿ በላይ በተደጋጋሚ ውክልናቸው ያስጠሯት ሁለት ዳኞች ናቸው። ኢንተርናሽናል አርቢትሮቿ ሊዲያ ታፈሰና በአምላክ ተሰማ…..አሁን ግን ኢትዮጵያ ውክልናዋ በአንዱ ያውም በበአምላክ ተሰማ ብቻ ሊሆን ሰአታት ናቸው የቀሩት…
ባለፋት 23 አመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ የመሀል ሜዳዋ ንግስት ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ ነገ የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮዽያ ቡና ጨዋታ ከመጀመሩ 5 ደቂቃ በፊት በዲ ኤስ ቲቪ ሽፋን በሚያገኝበት ሂደት ከለመደችው መድረክ በክብር ትሸኛለች። ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ “በሲዳማ ደርቢ” በክብር በተሸኘበት መድረክ የአዲስ አበባ ዳኞች በኢንተርናሽናል አርቢትር በላይ ታደሰ አስተባባሪነት እንዲሁም ሌሎች የሙያ ጓደኞቿና “የሸገር ደርቢ” እድምተኞች ባሉበት ነገ ለሊዲያ የክብር ሽኝት ይደረጋል….
በቀጣይ አርቢትሯ በኮሚሽነርነት የምትመለስ ሲሆን ሴት ዳኞችን በማብቃቱ ስራ ላይ ያላትን ልምድ እንድታካፍል የሚመለከታቸው አካላት ሊያስቡበት ይገባል… የነገው ጨዋታ ከሚፈጥረው ግለት በተጨማሪ የአርቢትሯ ሽኝት ሌላ ተጨማሪ ውበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል…..