የዋሊያዎቹ አዲሱ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል
ገ/ማሪያም የብሄራዊ ቡድኑ አባላት ከአፍሪካ ዋንጫ መውደቃችንን አውቀውም ቢሆን ላሳዩት ዲሲፕሊን ማመስገን እፈልጋለሁ” ሲሉ ተናገሩ።
አሰልጣኝ ዳንኤል በሀላፊነታቸው ስር የመጀመሪያው የሆነውን የማጣሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት ካጠናቀቁ ከቀናት በኋላ ዛሬ በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ በሰጡት መግለጫ “ማላዊ ጋር ከተካሄደው ጨዋታ አስቀድሞ ከአርባምንጭ ከተማ ያደረግነው የልምምድ ጨዋታ እንጂ የወዳጅነት ጨዋታ አይደለም ይሄ መስተካከል አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።
” ከአርባምንጭ ከተማ ያደረግነው የልምምድ ጨዋታ እንጂ የወዳጅነት ጨዋታ አይደለም ከዚያ ተነስተን ከማላዊ ጋር ባደረግነው ግጥሚያ ያረምናቸው ወደ ፊት የምናርማቸው ክፍተቶች አሉ” ያሉት አሰልጣኙ
“የቡድናችን ጠንካራ ጎን የሚሰጣቸውን ስልጠና የመተግበር በጋራ ያላቸው መተባበርና መቀባበል ሲሆን
ደካማ ጎኑ ደግሜ የመጨረስ ችግራችን አሁንም ታይቷል በቀጣይ ሶስተኛ ሜዳ ላይ ያለው የአጨራረስ ችግራችንን ለመቅረፍ እንጥራለን የፌዴሬሽናችን ም/ል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳኛቸውም በክፍል ውስጥ የስነ ልቡና ትምህርት ሰጥተውልናል” በማለት ተናግረዋል።
“የቴክኒክ ዳይሬክተር እንደመሆኔ ወጣቶችን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ለማጫወትም አቅደን አሳክተናል
ከወራቶች በፊት በማላዊ 2ከ1 የተረታንበትን ጨዋታ ከተጨዋቾቼ ጋር ሆነን አይተናል በጨዋታው በተጋጣሚ ሜዳ ላይ ጫና አድርገን በመጫወት በአጨዋወት ደረጃ የምንፈልገውን አድርገናል ነገር ግን 3 ነጥብም ለማሳካት ተጉዘን ያገኘነው 1 ነጥብ ሆኗል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።