By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጨዋታ ዘገባ | ለገጣፎ ለገዳዲ ሲዳማ ቡናን አሸንፏል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሲዳማ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሲዳማ ቡናየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግለገጣፎ ለገዳዲ

የጨዋታ ዘገባ | ለገጣፎ ለገዳዲ ሲዳማ ቡናን አሸንፏል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 3 years ago
Share
SHARE

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ29ነኛ ሳምንት ጨዋታ ሶስተኛ ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ በጥሩ መሻሻል ላይ ይገኝ የነበረዉን ሲዳማ ቡና 3ለ2 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

ከመርሐግብሩ መጀመር አስቀድሞ በርካቶች ለሲዳማ ቡና የማሸነፍ ቅድመ ግምት በሰጡበት ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ሀያ ያህል ደቂቃዎች ባልተጠበቀ መልኩ ለገጣፎ ለገዳዲ በጨዋታዉ ተሽለው ሲንቀሳቀሱ በሙከራ ረገድም በ18ተኛዉ ደቂቃ ላይ የፊት መስመር ተጫዋቹ ቴዲ ንጉሱ በከተፈራ አንለይ የተሻገረለትን ኳስ በቀታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም በግብ ዘቡ አዱኛ ፀጋየ አማካኝነት ኳሷ ግብ ከመሆን መክናለች።

ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ለገጣፎ ለገዳዲ ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም በ21ኛዉ ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻማዉን ኳስ ቁመተ መለሎዉ አጥቂ ካርሎስ ዳምጠዉ በግንባሩ በመግጨት ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

- ማሰታውቂያ -

በተቃራኒው በጨዋታው ደካማ አጀማመር ያደረጉት ሲዳማዎች በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ በለገጣፎ ብሎጫ ተወስዶባቸዉ ግብ ለማስቆጠርም ሆነ ለግብ የቀረበ ሙከራ ለማድረግ ሲቸገሩ ሲስተዋል በ27ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን በአጋማሹ ተጠቃሽ ሙከራን በአማካዩ አበባየሁ ዮሀንስ አማካኝነት ማድረግ ችለዋል። በዚህም በጥሩ ቅብብል ከመሐል ክፍል የተቀበለዉን ኳስ አማካዩ ከርቀት በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም የግብ ዘቡ ኮፊ ሜንሳህ እንደምንም መልሶበታል።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም አጋማሹ ሊጠናቀቅ አራት ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩ በ41ኛዉ ደቂቃ ላይ መሪነታቸዉን ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም ግብ ጠባቂዉ አዱኛ ፀጋየ የመለሰዉን ኳስ አጥቂዉ አማኑኤል አረቦ በአስደናቂ እይታ ወደ ግብነት በመቀየር የክለቡን መሪነት ወደ ሁለት ለዜሮ ከፍ ማድረግ ችሏል።

ከዕረፍት መልስ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ በማስገባት ወደ ጨዋታው ለመመለስ የሞከሩት ሲዳማዎች በጥሩ የመሐል ሜዳ እንቅስቃሴ በጨዋታዉ አደጋ ለመፍጠር በሚጥሩበት ወቅት በ62ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሶስተኛ ግብ ተቆጥሮባቸዋል። በዚህም የፊት መስመር ተጫዋቹ ሱለይማን ትራኦሬ ለራሱ የመጀመሪያውን ለክለቡ ደግሞ ሶስተኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ገና በጨዋታዉ 60 ያህል ደቂቃዎች ሳይጠበቅ በለገጣፎ ሶስት ጎል ያስተናገዱት ሲዳማዎች ደግሞ በ70ኛዉ ደቂቃ ላይ ወደ ጨዋታዉ የሚመልሳቸዉን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም ተከላካዩ ያኩቡ መሐመድ ከርቀት አክርሮ ወደ ግብ የላካት ኳስ የግብ ጠባቂዉ ኮፊ ሜንሳህ መረብ ላይ አርፋለች።

ወደ ጨዋታዉ የሚመልሳቸውን ግብ ማስቆጠር ከቻሉ በኋላ ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቀጠሉት ሲዳማዎች በ79ነኛዉ ደቂቃ ላይ በግራ ተከላካዩ መሐሪ መና አማካኝነት ድንቅ ሙከራ አድርገዉ በድጋሚ ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ በ86ተኛዉ ደቂቃ ደግሞ በዚሁ ተጫዋች አማካኝነት ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ጫና ፈጥረዉ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዉ በለገጣፎ ለገዳዲ 3ለ2 በሆነ ዉጤት የተሸነፉ ሲሆን በጨዋታዉ መገባደጃ ወቅትም የለገጣፎዉ አጥቂ ሱለይማን ግብ ጠባቂዉ አዱኛ ፀጋየ ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የጨዋታ ዘገባ | አፄዎቹ ደረጃቸዉን ማሻሻል የቻሉበት ዉጤት አስመዝግበዋል !!
Next Article የጨዋታ ዘገባ |ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረዉ የሊጉ ሻምፒዮን መሆን የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዋልያዎቹዜናዎችካታር 2022

የዋልያዎቹ ጨዋታ ይራዘም ይሆን ?

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 5 years ago
የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ባህር ዳር ከነማ ከ አዳማ ከተማ
“እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ ሆኜ ሳይሆን በተጨዋችነት ሜዳ ውስጥ ግብጽን መፋለም እመርጥ ነበር” ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማሪያም / አዲሱ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ /
ሁለተኛ የውድድር ቀኑን የያዘው ትግራይ ዋንጫ ዛሬ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ውሏል 
ከ23 አመት በታች የሴካፋ ሻምፒዮና በኢትዮጵያና በኤርትራ ጨዋታ ዛሬ በይፋ ይጀመራል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?