በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአስራ ሰባተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ ባሳለፍነዉ ሳምንት አራተኛ ተከታታይ የአቻ ወጤት ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና እና በተቃራናዉ ባሳለፍነዉ ሳምንት ለገጣፎ ለገዳዲን አንድ ለዜሮ ማሸነፍ የቻለዉ ሀዋሳ ከተማ ጨዋታቸውን ያለ ግብ በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።
አዳሩን በድሬዳዋ ከተማ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ለመጫወት ትንሽ አስቸጋሪ በነበረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የመጀመሪያ አስራ አምስት ደቂቃዎች ያህል ቡናማዎቹ የተሻለ መንቀሳቀስ የቻሉ ሲሆን በተለይ ደግሞ በፊት መስመር አጥቂያቸዉ ብሩክ በየነ እና በተከለካዩ ራምኬል ጀምስ የግንባር ኳስ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል።
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃ ላይ በጥሩ የአጨዋወት መንገድ ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ የቻሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች የነበሩ ቢሆኑም በተደጋጋሚ በተለይ ደግሞ በጨዋታው የመጀመሪያ አስራ አምስት ያህል ደቂቃ ጫና ውስጥ ገብተዉ የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች በመልሶ ማጥቃት እና በመስመር በኩል ከሚነሱ ኳሶች ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ በስተዋልም ነገር ግን ተጠቃሽ ሙከራን ለማድረግ 40 ያህል ደቂቃ መጠበቅ ግድ ብሏቸዉ ነበር ፤ በዚህ ሂደት የቀጠለዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም ከሜደዉ ምቹ አለመሆን ጋር ተዳምሮ ቡድኖቹ ለመጫወትም ሆነ ግብ ለማስቆጠር ሲቸገሩ ተስተውሏል።
በዚህም በ40ኛዉ ደቂቃ ላይ የሀይቆቹ የፊት መስመር አጥቂ ሙጅብ ቃሲም ከሳጥን ውጭ አክርሮ ወደ ግብ የላካት ኳስ በአጋማሹ በሀይቆቹ በኩል የተደረገች የመጀመሪያ ሙከራ ሁናለች።
ያን ያህል ተጠቃሽ ለግብ የቀረበ ሙከራ ባልተስተዋለበት የመጀመሪያው አጋማሽ ቡናማዎቹም ሆነ ሀዋሳ ከተማዎች ከሳጥን ውጭ እንዲሁም ከቆሙ ኳሶች ከሚደረጉ ሙከራዎች ዉጭ አስደንጋጭ ሙከራ ሳያስመለክቱን ሁለቱ ቡድኖች ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከዕረፍት መልስ በመጠኑም ቢሆን ሁለቱም ቡድኖች በእንቅስቃሴ ተሻሽለዉ ወደ ሜዳ ሲመለሱ ነገር ግን በሙከራ ረገድ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሲቸገሩ ተስተውሏል። በዚህ ሂደት እየቀጠለ በነበረዉ ጨዋታም በ59ነኛዉ ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናዉ አምበል አማኑኤል ዮሐንስ በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ከዚህ ክስተት በኋላ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የቁጥሩን ብልጫ ለመጠቀም የማጥቃት ባህሪ ያለቸዉን ተጫዋቾች ቀይረዉ ያስገቡት ሀይቆቹ አሁንም ከሜዳዉ አለመመቸት ጋር ተያይዞ ግብ ለማስቆጠር አልያም ለግብ የቀረበ ሙከራን ለማድረግ ሲቸገሩ ተስተውሏል። ይልቁኑንስ በ74ተኛዉ ደቂቃ ላይ ቡናማዎቹ በመሐመዴ ኑር አመከኝነት ግብ ለማስቆጠር ተቃርበዉ የነበረ በህንም ሳይሳካላቸዉ ቀርቷል። በዚህ ሂደት የቀጠለዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ግን ሙሉ ዘጠና ደቂቃዉ ተጠናቆ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ድንቅ ለግብ የቀረበ ሙከራ ተስተዉሎበታል። በዚሀም የቡናማዎቹ ተከላካይ አንተነህ ያሻማዉን ኳስ ሮቤል በግንባሮ ገጭሎ ግብ ለማስቆጠር ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም በግብ ዘቡ አለዛር አማካኝነት ሳይሳካለት ቀርቶ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል።