► 2.4 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል
► በጥናቱ 90 ሰዎች ኢንተርሺው ተደርገዋል
► የ140 ሀገራት ልምድ ተዳሷል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ገና ከምስረታው ራሱን ማወቅና ያለበትን ደረጃ መረዳት ላይ ትኩረት አድርጎ ሊጉን የማስጠናት ስራ እንደሰራ አስታወቀ።
“ዘርፈ ብዙ የግምገማ ጥናትና የልማት ፍኖተ ካርታ” በሚል የተደረገው ጥናት ከነገ በስቲያ ረቡዕና ሃሙስ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የሚቀርብ ሲሆን ዛሬ በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቦርድ ፕሬዝዳንቱ መቶአለቃ ፈቃደ ማሞ እንደተናገሩት “የሀገሪቱ እግርኳስ የደረሰበት ደረጃ ያለበት እውነት ያለው ሀብት በተመለከተ ጥናት ተደርጓል። መፍትሄ የሚያመጣ ችግራችንን የሚያስወግድ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን ከኢትዮጵያ ቡናና ከቅዲስ ጊዮርጊስ ውጪ አካውንት አልነበራቸውም አሁን ግን ሁሉም አላቸው እያስተማርን እያስገደድን ለውጥ እንዲመጣ እናደርጋለን ጥናቱ ለውጥ ያመጣል ካልን ሁሉም አካላት እንዲቀበሉት በጥናቱ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ሲምፖዚዮሙ ላይ እናስተምራለን 16ቱ ክለቦች የሚገኙባቸው ክልሎች ርዕሰ መስተዳደሮችን የማስረዳት ትዕዛዝ እንዲሰጡ ለማድረግ እንጥራለን ጥሪ ያደረግነው ጉዳዩ ለሚያዙና ለሚፈጽሙ በመሆኑ ሚዲያውም አግዞን የተሻለ ስራ ይኖረናል ብዬ አስባለሁ ጥናቱ ከተተገበረ የሀገሪቱ እግርኳስ ለውጥ ማየታችን ርግጠኛ ነኝ” ሲሉ ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
” ጥናቱ ይጠና ብለን ጨረታ ስናወጣ ሰባት ተቋማት መጥተዋል አየርመንገድና ቴሌን ያጠኑ ሁሉ መጥተው በዶክተር ጋሻው የሚመራው ተቋም አሸንፎ ጥናቱ ተካሂዷል ይሄ ጥናት የሚቀጥለው ትውልድ በተቀመጠ ሰነድ ላይ እንዲመራ በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ ያለውን ሂደት ችግርና መፍትሄ የሚገልጽ ጥናት ተደርጓል ተቋማችንም ጠንካራ እንደሚሆን አምናለሁ ጥናቱ ረጅም ጊዜ ቢወስድም ይህን ጥናት የፈቀዱ አካላትን አመሰግናለሁ ለሲምፖዚየሙ 220 ሰው ተጠርቷል የተወካዮች ምክር ቤት የስፖርት ዘርፍ፣ ስፖርቱን የሚመሩ ሚኒስትርና ደኤታዎች፣ የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች የስፖርት ኮሚሽን ሃላፊዎች፣ ኮሚሽነሮች የ16ቱ ክለቦች ፕሬዝዳንቶች ስራ አስኪያጆችና አሰልጣኞች፣ ዳኞች፣ ኤጀንቶች፣ 6 ዩኒቨርስቲዎች ጠርተናል ጥናቱ ላይ ውይይት አድርገን ስንጨርስ ለኢትዮጵያ እግርኳስ መፍትሄ እንደሚሆን አምናለሁ ለዚህ ጥናትና ለረቡዕና ሃሙስ ሲምፖዚየም 2.4 ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረግነውም ጥናቱ ወሳኝ በመሆኑ ነው” በማለት የሊግ ኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጆ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል።
ጥናቱን ያደረጉት ዶክተር ጋሻው በዙ በበኩላቸው እንደገለጹት “ጥናቱ የሊጉ አጠቃላይ ገጽታ፣ የሊጉ ነባራዊ ሁኔታ፣ ተቋማዊ እሴት፣ የአሰራር ስርአትና የአመራር ሂደት፣ የፋይናንስና የገቢ አስተዳደር ፣ የሚወርዱና የሚወጡ ክለቦች፣ የተጨዋቾች ደመወዝ አከፋፈል ሂደት ተጠንቷል.. ጥናቱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና ሊጉ ልዩነትና አኔድነትን ዳሰናል። በሊጉና በፌዴሬሽኑ መሃል ያለው አንድነትና ልዩነት ላይ ምክረ ሀሳብ አቅርበናል
ሁለቱም ተቋማት መስመር እንዲሰመርላቸው የሚፈልጓቸውን የዳኞችን አስተዳደር ፣የአሰልጣኞች አስተዳደርና የተጨዋቾች ቅጥርና ዝውውር ላይ መፍትሄ የሚያመጣ ምክረ ሃሳብ አቅርበናል ለዚህ ሲባል የ14 አገራትን ልምድ መርምረናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር ጋሻው እንዳስረዱት ” ለዚህ ጥናት 15 ባለድርሻ አካላትን አነጋግረናል 90 በቀጥታ ያገባቸዋል የተባሉ ግለሰቦች ቃለመጠይቅ ተደርጓል የ140 አገራት ተሞክሮ ፣ 300 ሳይንሳዊ ጥናታዊ ጽሁፎች ፣46 ምክረ ሃሳብና 6 አማራጭ መንገዶች ተቀምጠዋል አጠቃላይ ጥናት የክለቦች የባለቤትነት ይዞታ፣ የስራ ፈቃድ፣
የራስ ገዝነት/ ራሳቸውን ችለዋል ወይ?/የሚለው የአሰራርና የፋይናንስ ሂደቶች የአጥኚው ተቋም ምክረ ሃሳብ የቀረበባቸው ጉዳዮች ናቸው” ሲሉ አብራርተዋል።
220 ሰው የሚታደምበት የሁለት ቀኑ የኢንተርኮንቲኔንታሉ ሲምፖዚየም ከነገ በስቲያ ረቡዕና ሃሙስ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል