የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታድየም መደረግ ይጀምራሉ ።
የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ በሐዋሳ ከተማ አመሻሽ ላይ እየጣለ በሚገኘው ዝናብ ምክንያት የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚጀምሩበት ሰዓት ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል ።
በዚህም በ9:00 ሰዓት እንዲጀምሩ ፕሮግራም የወጣላቸው ጨዋታዎች በሙሉ በ7:00 እንዲሁም በ12:00 ሰዓት ይጀምሩ የነበሩ ጨዋታዎች ደግም በ10:00 ሰዓት የሚጀምሩ ይሆናል።
በተጨማሪም ጨዋታውተጀምሮ በዝናብ ምክኒያት የተቋረጠ ጨዋታ ካለ ጨዋታው በማግስቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ አርተፊሻል ሜዳ ላይ እንዲጠናቀቅ ኮሚቴው ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በነገው ዕለት ሲጀምሩ 7:00 ሲዳማ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም 10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከለገጣፎ ለገዳዲ ይጫወታሉ ።