በ19ኛው የአለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የ2ኛው ዙር ተጓዦች ዛሬ አመሻሽ ላይ ሽኝት ተደርጎላቸዋል ።
በሽኝት መርሃ-ግብሩ ላይ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ የሆነው የኢትዮጵያ አትሌትክስ ደጋፊዎች ማህበር በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በመገኘት የመልካም ምኞት መግለጫና የሽኝት ኬክ በመቁረስ ለሁሉም የልዑካን ቡድኑ አባላት አድርጓል ።
በአሸኛኘቱ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር የስራ አስፈፃሚዎች የተገኙ ሲሆን ከብሔራዊ ቡድን ተጓዥ አትሌቶች እና ልዑካን ቡድን ጋር የኬክ መቁረስ ፕሮግራም አካሄደዋል ።
- ማሰታውቂያ -
በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚና አቃቢ ንዋይ የተከበሩ አቶ ተፈራ ንዋይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድኑን የሚደግፍ ማህበር በመኖሩ ደስተኛ እንደሆኑና ባለፈው አመት ከኦሪገኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መልስ የተደረገውንም አቀባበል በማንሳት አመስግነዋል።
በመርሐግብሩ ላይ ረ/ኮሚሽነር አትሌት ማርቆስ ገነቲ፣ ወ/ሮ ሳራ ሃሰን፣ አትሌት መሠለች መልካሙ፣ የፅ/ቤት ተወካይ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝና አቶ አስፋው ዳኜ የቡድኑ ረ/የቴክ/መሪ በስፍራው በመገኘት ለልዑካን ቡድኑ አባላት መልካም እድል በመመኘት አሸኛኘት አድርገዋል ።
በዚህኛው ዙር የተሸኙት በ1500ሜ ሁለቱም ፆታ ፣ 3000ሜ መሰነክል ወንዶች እና 10,000ሜ ሁለቱም ፆታ አትሌቶች ፣ አሰልጣኞች፣ የቡድኑ ሚድያ ተጠሪ፣ ኦፊሻሎች፣ የህክምና ባለሞያዎች፣ እንዲሁም ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ረዳት የቡድን መሪ፣ አቶ አሰፋ በቀለ የቴክኒክ ቡድን መሪን ጨምፎ በአጠቃላይ 35 የልዑካን ሽኝት ተደርጎላቸዋል ።
የቡድን አባላት ዛሬ ረብዑ ነሃሴ 10/2015 ከሌሊቱ 5:40 ላይ ውድድሩ ወደሚደረግበት ቡዳፔስት ከተማ በረራቸውን ያደርጋሉ ።