ኢትዮጵያን ወክሎ በሴካፋ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድባንክ የሴቶች ቡድን ሁለተኛ ጨዋታውን በዛሬዉ ዕለት አድርጎ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል ።
በዚህም ከቀናት በፊት በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ የቡሩንዲውን ቡጃ ኩዊንስ 2ለ1 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ የቻለዉ እና በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታውን ከጅቁቲዉ ከፋድ እግርኳስ ክለብ ጋር ያደረገዉ ንግድ ባንክ 8ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግሎችም የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ ፣ ሲናፍ አወል (ሁለት) ፣ አረጋሽ ካልሳ ፣ ናርዶስ ፣ እፀገነት እና አርያት ኦዶንግ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ። ኢትዮጵያ ንግድባንክ የምድቡን ሶስተኛ ጨዋታም ከቀናት በኋላ ከዩጋንዳዉ ካምፓላ ኪውንስ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።