የ2015 ዓመተ ምህረት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ይሳተፋል ።
በትናንትናው ዕለት ይፋ በተደረገው የቅደመ ማጣሪያ ድልድልም ከዛንዚባሩ “KMKM” ጋር መደልደሉ ይታወሳል ።
የቅደመ ማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ የሚያደርጉት ፈረሰኞቹ በመጪው ሰኞ ቢሾፍቱ በሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩ ይሆናል ።
ቀዳሚው ከሜዳ ውጪ የሚደረገው ጨዋታ ከነሐሴ 12 – 14 ሲደረግ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከነሐሴ 18 – 20 ባሉት ቀናት መካከል ይደረጋል ።