በአሰልጣኝ አስራት አባተ እየተመሩ ለቀጣይ የዉድድር አመት ራሳቸዉን ለማጠናከር ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀለ የሚገኙዉ የምስራቁ ተወካይ ቡድን ድሬደዋ ከተማ ተከላካይ ማስፈረም ችሏል።
ከዚህ ቀደም ደደቢት፣ ወልዲያ እና ሀምበሪቾ ዱራሜ በመጫወት ያሳለፈዉ እንዲሁም ያለፈዉን የዉድድር አመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጫወተዉን ዳግማዊ አባይን አስፈርሟል፤ተጫዋቹ በድሬዳዋ የሁለት አመት ኮንትራት ፈርሟል።
ዳግማዊ አባይ ለድሬደዋ ስድስተኛ ፈራሚ በመሆን ተመዝግቧል።