ሲዳማ ቡና ውጤታማ የጎል አዳኝ በመሆን ኢትዮጵያ ከምትጠራቸው አጥቂዎች አንዱ የሆነውን ጌታነህ ከበደን ለማስፈረም ተስማማ።
ከደቡብ ፖሊስ የተነሳው የአስር አለቃ ጌታነህ ከበደ
/ ሰበሮም/ የከፍታ ጉዞ በደደቢት፣ በቅዱስ ጊዮርጊስና በወልቂጤ ከተማ በግብ ቀበኝነቱ ከክለብ አልፎ ወደ ዋሊያዎቹ ዘልቆ አጥቂው ዘንድሮ በሊጉ ሁለተኛ ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆኖ መጨረሱ ይታወቃል።
በዘንድሮ የሊግ ውድድር ላለመውረድ የመጫወት ግዴታ ውስጥ ገብቶ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ከመውረድ የተረፈው የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ሲዳማ ቡና ገና ከአሁኑ ራሱን እያጠናከረ ሲሆን የቡድኑን አጥቂ ይገዙ ቦጋለ ኮንትራትን ከቀናት በፊት ማራዘሙ ይታወሳል።
ሲዳማ ቡና ከአሜሪካ ከተመለሰው ጌታነህ ከበደ ጋር በመስማማቱ በቀጣዮቹ ቀናት ፌዴሬሽን ጽ/ቤት በመሄድ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።