በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት እና ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዉድድር ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የናይጄሪያ ዜግነት ያለዉን የመስመር የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል።
ፈረሰኞቹ በዝዉዉሩ መስኮት በንቃት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከእሱ ጎን ለጎን የነባር ተጫዋቾቻቸዉን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ በሁለት ዓመት ኮንትራት ናይጄሪያዊዉን አጥቂ ሞሰስ ኦዶ ቶቹኩን የግላቸዉ አድርገዋል።
ተጫዋቹ ባሳለፍነዉ አመት ከነበረበት የሱዳኑ ክለብ ሜሪክ ጋር ለዝግጅት ወደ ኢትዮጵያ ደብረ ዘይት በመጣበት ወቅት በቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኞች እይታ ዉስጥ መግባት የቻለ ሲሆን በስተመጨረሻም ክለቡ ከተጫዋቹ ጋር ንግግር አድርጎ ተጫዋቹ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊሆን ችሏል።