በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት እና ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዉድድር ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የጋና ዜግነት ያለዉን የተከላካይ አማካይ የመሀል ሜዳ ተጫዋች አስፈርመዋል።
ፈረሰኞቹ ክዋሜ አዶም ፍሪምፓንግን በሁለት ዓመት ኮንትራት የግላቸዉ ማድረግ የቻሉ ሲሆን ጋናዊዉ የተከላካይ አማካይ በዪፋ ፈረሰኞቹን ለመቀላቀል የወረቀተ ስራዎች ብቻ ይቀሩታል።