የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ማህበር የ2015 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ እግርኳስ ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ ወጣት ተጫዋች አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል ።
ማህበሩ ከእያንዳንዱ ክለብ አምበሎች ሰበሰብኩት ባለው ድምፅ መሰረት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቢንያም በላይ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል ።
ቢንያም በላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ የውድድር ዓመት ቆይታው በወጥነት ጥሩ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በማሳየት ለክለቡ ሻምፕየንነት ትልቅ ሚና ከተወጡት ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደነበር ይታወቃል ።
በተጨማሪም የአዳማ ከተማው አጥቂ ዮሴፍ ታረቀኝ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል ።
- ማሰታውቂያ -
በውድድር አመቱ ባሳዩት የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የሊጉን ተከታታዮች ቀልብ መሳብ ከቻሉ ወጣት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ዮሴፍ ታረቀኝ እንደነበረ የሚታወስ ነው ።