ፍጻሜውን ሳያገኝ የቆየው የ2015 የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ የደረጃና የፍጻሜ ጨዋታ የፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው ።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ መድን የሚያደርጉት የደረጃ ጨዋታ ረቡዕ 7 ሰዓት 9.30 ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ከሃድያ ሆሳዕና ደግሞ የዋንጫ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ውድድሩ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የቦታ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተብሎም ተገምቷል።