መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን የ15ሺ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ የ10ሺ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

ኢትዮጵያ መድን የ15ሺ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ የ10ሺ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል

አጋራ
አጋራ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች !!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና አመራር ስነስርዓት ኮሚቴ በአንደኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎችን በተመለከተ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።

#በተጫዋቾች_ደረጃ:- የድሬዳዋ ከተማዉ ኤልያስ አህመድ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ለፈፀመው ጥፋት 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ሶስት ሺ ብር እንዲከፍል እንዲሁም ጊት ጋትኩት ፣ ሽመክት ጉግሳ ፣ ዊሊያም ሰለሞን ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀም ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ሲሆን በዚህም 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ተወስኗል።

የድሬዳዋዉ እንየው ካሳሁን ሃይማኖታዊ መልእክት የሚያስተላልፍ ምስል በውስጥ ልብሱ ደርቦ ስለመልበሱ ሪፖርት የተደረገበት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ተጫዋቹ ሶስት ሺ ብር እንዲከፍል ሲቀጣ እንዲሁም ክለቡ ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ አስር ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል።

#በክለብ_ደረጃ :- ድሬደዋ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በመመሪያዉ መሰረት አምስት ሺ እንዲከፍል ፣ ኢትዮጵያ መድን ባደረገው ጨዋታ ከዕረፍት መልስ የክለቡ ተጫዋቾች 4 ደቂቃ ወደሜዳ ዘግይተው በመግባሃቸዉ አስራ አምስት ሺህ ብር እንዲከፍል እንዲሁም በዚህ ምክኒያት የቀጥታ ቴሌቭዥን ስርጭት መብት የገዛው ድርጅት የአክሲዮን ማህበሩን የካሳ ክፍያ ከጠየቀ የተጠየቀውን ክፍያ እንዲከፍል ተወስኖባቸዋል።

በተጨማሪም ወልቂጤ ከተማ ባደረገው የሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ተጫዋች ሳሙኤል አስፈሪ ከተፈቀደው የመለያ ቁጥር/1-50/ ውጪ 66 ቁጥር ለብሶ ስለመጫወቱ ሪፖርት የተደረገበት በመሆኑ በደንቡ መሰረት ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ሶስት ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...