በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ እንዲሁም የነባር ተጫዋቾችን ዉል እያደሱ ለ2016 ዓ.ም ለቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅድመ ዝግጅታቸዉን እየሰሩና ከፍለፊታቸዉ ላለባቸዉ ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እራሳቸዉን እያዘጋጁ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የመስመር ተከላካይ አስፈርመዋል።
ፈረሰኞቹ ከሲዳማ ቡና የተስፋ ቡድን የተገኘዉን እና ያለፉትን 7 ዓመታት ከሲዳማ ቡና ጋር ያሳለፈዉን አማኑኤል እንዳለን በዪፋ በሁለት ዓመት ኮንትራት ወደስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።