የሊጉ ግርጌ ላይ ሚገኘው ደደቢት ተጨዋቾቹ የ4 ወር ና ከዛ በላይ ደሞዝ እለመከፈላቸውን ተከትሎ የቀኑ መደበኛ ልምምዳቸውን ዛሬ ሳይሰሩ ቀርተዋል።በውድድር ዓመቱ መጀመርያ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞት የነበረው ደደቢት ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚሞክርበት ሰዓት እንዲህ እይነት ችግር መከሰቱ ከወራጅ የመውረድ ዕድሉ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል።
በሁለተኛው ዙር በዳንኤል ፀሃየ እየተመራ ሁለት ጨዋታዎችን በማሸነፍ መነሳሳትን ያሳየው ደደቢት የተጨዋቾቹ ልምምድ ማቆም የቡድኑ ውጤቱ ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳድር መገመት ቀላል ነው።
በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በሜዳው በድሬዳዋ ሽንፈት ያስተናገደው ደደቢት በሚቀጥለው ሳምንት በትግራይ ስታድየም ጅማ ኣባጅፋርን እሚያስተናግድ ይሆናል።