በአሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ እየተመሩ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል የቻሉት ድሬዳዋ ከተማዎች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ጋናዊ ተከላካይ ማስፈረማቸዉን ይፋ አድርገዋል።
ከዚህ ቀደም ለጊኒዉ ሆሮያ ክለብ ፣ ለጋናዉ ድሪምስ እና ለሳውዲ አረቢያዉ አል ሻርቅ መጫወት የቻለዉ ተከላካዩ አሳንቴ ጋድፍሬድ አሁን ደግሞ አንድ አመት በሚቆይ የስምምነት ውል ብርቱካናማዎቹን መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።