*….የወራት ደመወዝ ሳይከፍሉ ተጨዋቾችን ማስፈራራት የማይቻልበት ዘመን መጥቷል….
ፋሲል ከነማ የሀምበሪቾ ዱራሜውን አጥቂ አፍቅሮት ሰለሞንን ማስፈረሙን ከክለቡ የውስጥ አዋቂ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
በሀምበሪቾ በዘንድሮ የውድድር አመት የአንድ ወር ደመወዝ ብቻ የተከፈለው አፍቅሮት ከፋሲል ከነማ የቀረበለትን ጥሪ በመቀበል አንድ አመት ከስድስት ወር ፊርማውን ለአጼዎቹ አኑሯል።
ከ3 ወር በላይ ደመወዝ ካልተከፈላቸው ተጨዋቾች መሃል የሚገኘው ተጨዋቹ ለፌዴሬሽኑ ያቀረበውን ጥያቄ ፌዴሬሽኑ ተቀብሎ ዝውውሩን አጽድቆታል። ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተገኘ መረጃ ከ2 ወር በላይ ደመወዝ ያልተከፈላቸው ተጨዋቾች በህጋዊ መስመር ለክለቡ ጥያቄ በማቅረብ መልስ ካጡ መብታቸውን ለማስከበር የሚያደርጉትን ጥረት በህጋዊነት በመቀበል በውላቸው መሰረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾችና አፍሪካዊያን ተጨዋቾች እኩል የማይታዩበት ዘመን ከዚህ በኋላ እንደማይኖርና ተጨዋቾች በውላቸው መሰረት ካልተስተናገዱ አስፈላጊ እርምጃ ስለሚወስድ ሁለቱም ወገኖች መብትና ግዴታቸውን እንዲያከብሩ ጠይቋል።
ይህም ውል እያላቸው ደመወዝ ባለመከፈሉ ዝውውር እንዲያደርጉ ከተፈቀደላቸው የአዳማዎቹ ሀይደር ሸረፋና ተክለማሪያም ሻንቆ /ጎሜዝ/ በመቀጠል አፍቅሮት ሰለሞን ሶስተኛው ተጨዋች ሆኗል።