ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን የኢትዮዽያ ቡናው ምክትል አስልጣኝ ዘላለም ጸጋዬ እንግዳችን ነው… በርካታ ጉዳዮችን ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያወጋው አሰልጣኝ ዘላለም ” የቀጠረኝ ኢትዮዽያ ቡና ነው እያገለገልኩ ያለሁት ግን ካሳዬን ነው” ሲል ተናግሯል…ፊት ለፊት ተናጋሪው ዘላለም ” 130 ሺህ ብር ደመወዝ እየተከፈላቸው እነሱን በጊዜ ግቡ ሂዱ ኑ ማለት ጊዜው አይፈቅድም”ሲል ተጨዋቾች ፕሮፌሽናል የሆነ አስተሳሰብ ሊኖራቸው እንደሚገባ መክሯል።
*…የቅዱስ ጊዮርጊሱ ደስታ ደሙ”ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስትመጣ ቀድመህ ማለም ያለብህ ብርን ሳይሆን ስኬትን ነው” ሲል ይናገራል….
- ማሰታውቂያ -
*…. አጫጭር ዜናዎችን ይዘናል….
*… ወደ ፕሪሚየር ለማደግ ሀዋሳ ላይ እየተፋለሙ ስላሉትና እድል ስላላቸው ሶስቱ ክለቦች….
*….የውጪ ግብ ጠባቂ ገደብ አለመደረጉ….
*…ስለተከፈተው የዝውውር መስኮትና ሌሎች ዜናዎች ተካተዋል።
*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….
*….. ተጠራጣሪዎቹን አፍ ስላዘጋው የሶስቱ አናብስት የቁርጥ ቀን ልጅ ሃሪ ኬን ዙሪያ ያዘጋጀነው ዘገባ አለ…..
*…” በአውሮፓ ዋንጫ ጥሩ ብቃቱን እያሳየ ያለው የእንግሊዙ ሉክ ሾው ” “በሮቤርቶ ካርሎስ መወደስ መቻል የሚያኮራ ነው” ሲል ተናግሯል …..
*…. ጣሊያንና እንግሊዝ ነገ ለእውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ይፋለማሉ…”የ2020 አስደናቂው የአዙሪዎቹ አስደናቂ ጉዞ የተዘጋጀ ዘገባም ተካቷል….
*…ጡረታ ከመውጣቱ በፊት ታሪክ መስራት ስላለመው የጣሊያኑ ማገር ጂዮርጂዮ ኬሌይኒ የተዘጋጀ ዘገባ አለን
*…. 47ኛው የኮፓ አሜሪካ ፍጻሜ ቅዳሜ ለሊት ለእሁድ አጥቢያ ይካሄዳል…በባርሴሎና ለአንድ አላማ ተፋጠው የነበሩት ጓደኛሞቹ ኔይማርና ሊዮኔል ሜሲ ብራዚልና አርጀንቲናን እየመሩ ይፋጠጣሉ….
*…..ክለቦችን ለከፍተኛ ወጪ ስላደረገው የተጨዋቾችጉዳት የምንለው አለ….
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……