ቀን 10 ሰዓት ሲል በዋና ዳኛ አባይነህ ሙላት ፊሽካ በጀመረው እና ተመጣጣኝ ፍክክር በተስተዋለበት የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ቶሎ ቶሎ ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል በመድረስ አደጋ ለመፍጠር ሲጥሩ የተስተዋለ ሲሆን ፤ በዚህም ሀዋሳ ከተማ በ17ተኛዉ ደቂቃ ላይ በአሊ ሱለይማን አማካኝነት ሙከራ ማድረግ ቢችሉም ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ ኳሷን መልሷታል።
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ በተቃራኒው ሻሸመኔ ከተማዎች በአሸናፊ ጥሩነህ አማካኝነት ሙከራ ቢያደርጉም ግብ ጠባቂዉ ፅዮን መርዕድ ተቆጣጥሮባቸዋል። በ36ተኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ አሊ ሱለይማን ከተባረክ ሄፋሞ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂዉ ሲመልስ በድጋሚ ያገኘዉ ተጫዋቹ ኳሷን ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።
በመጠኑም ቢሆን ብሎጫ የተወሰደባቸዉ ሻሸመኔዎች አጋማሹ ሊጠናቀቅ ሲል በሀብታሙ ንጉሴ አማካኝነት አስቆጪ ሙከራ ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም በ47ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን ተጨማሪ ግብ አስተናግደዋል። በዚህም በተመሳሳይ አማኑኤል ጎበና ያቀበለዉን ኳስ አሊ ሱለይማን ወደ ግብነት ቀይሮ የሀዋሳን መሪነት ወደ ሁለት ለዜሮ ከፍ አድርጓል ።
- ማሰታውቂያ -
ከዕረፍት መልስ በመጠኑም ቢሆን ተሻሽለዉ የተመለሱት ሻሸመኔዎች በ51ኛዉ ደቂቃ ላይ ከጌትነት ተስፋየ የተቀበለዉን ኳስ አሸናፊ ጥሩነህ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂዉ ፂዮን ሲያወጣበት በድጋሚ ከደቂቃዎች በኋላ ገዛኸኝ ደሳለኝ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ቢችልም ፂዮን ግን ኳሷን ተቆጣጥሯል።
በዚህም በ55ተኛዉ ደቂቃ ላይ በምንተስኖት አማካኝንት ግብ አስቆጥረዉ የተሻረባቸዉ ሻሸመኔዎች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ በ81ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥረዋል ፤ በዚህም አሸብሮ ውሮ ያሻማዉን ሷስ አጥቂዉ ስንታየሁ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል ። ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ በቀሩ ደቂቃዎች ጫናቸዉን አጠንክረዉ የቀጠሉት ሀይቆቹ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላ ሶስተኛ ግብ አስቆጥረዉ ጨዋታዉ 3ለ1 በሆነ ዉጤት በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ በቸርነት ጉግሳ ብቸኛ ግብ ተጋጣሚያቸዉን 1ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችለዋል ።
ምሽት 1 ሰዓት ሲል በጀመሩ የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች በተደጋጋሚ ወደ ተቃራኒ ቡድን የሜዳ ክፍል በመድረስ አደጋ ለመፍጠር ሲጥሩ የተስተዋለ ሲሆን በና በመባቻዉም ባህርዳር ከተማ በፍራኦል አማካኝንት ከቆመ ኳስ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችለዋል።
የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር እምብዛም ሙከራ ባላስመለከተዉ ጨዋታ በ35ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ታደሰ በጭንቅላቱ ድንቅ ኳስ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ኳሷን ተቆጣጥሯታል። በተደጋጋሚ ጫና ለመፍጠር ያልቦዘኑት መቻሎች በአጋማሹ መጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ጥሩ ዕድሎችን ቢፈጥሩም ግብ ሳያስቆጥሩ አጋማሹ ተጠናቋል።
በሁለተኛዉ አጋማሽም እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ እምብዛም ሙከራ ያልተመለከትን ሲሆን ነገር ግን በመቻል በኩል ሽመልስ በቀለ እንዲሁም በባህርዳር በኩል ፍሬዘር ካሳ እና ሀብታሙ ታደሰ ከቀኝ መስመር በኩል ወደ መከራ ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም ሁለቱም ክለቦች ሙከራቸዉን ወደ ግብነት መቀየር ሳይችሉ ቀርተዉ በጨዋታዉ መገባደጃ ወቅት ላይ በ83ተኛዉ ደቂቃ ግን ባህርዳር ከተማ በቸርነት ጉግሳ የጭንቅላት ግብ ጨዋታውን 1ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።