ሀዲያ ሆሳዕናዎች የቀድሞዉን የኢትዮጵያ መድን የመስመር ተከላካይ የነበረዉን አስጨናቂ ጸጋዬን በሁለት ዓመት ኮንትራት ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
አስጨናቂ ጸጋዬ ለአርባምንጭ ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ ፣ ጋሞ ጨንቻ እና ጅማ አባጅፋር የተጫወተ ሲሆን እንዲሁም ያለፈዉን የዉድድር ዓመት ከኢትዮጵያ መድን ጋር አሳልፏል።
ተጫዋቹ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በመገኘት ለሁለት አመት የሚያቆየዉን የውል ስምምነት ለሀዲያ ሆሳዕና አኑሯል።
ሀዲያ ሆሳዕናዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘዉ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ሆነዉ ዉድድራቸዉን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።