መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ፈረሰኞቹ በመጨረሻም ወደ ድል ተመልሰዋል !!
ሀዋሳ ከተማቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ፈረሰኞቹ በመጨረሻም ወደ ድል ተመልሰዋል !!

አጋራ
አጋራ

በዘጠነኛዉ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 3ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

በአራተኛው ሳምንት አዳማ ከተማን 2ለ1 በሆነ ዉጤት ካሸነፈ በኋላ በተከታታይ አራት ጨዋታዎች ማለትም በፋሲል ከነማ በአምስተኛዉ ሳምንት ሲሸነፍ በተከታታይ ከወልቂጤ ከተማ ፣ አርባምንጭ ከተማ እና መቻል ጋር ያደረገዉን ጨዋታዉ በአቻ ዉጤት ያጠናቀቀዉ የዘሪሁን ሸንገታዉ በመጨረሻም ወደ ድል ጎዳና የመለሰዉን ዉጤት ጠንካራዉ ሀዋሳ ተከማ ላይ ተቀዳጅቷል።

ከዛሬዉ ጨዋታ በፊት በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድም ሽንፈት ያልገጠመዉ እና ባሳለፍነው የጨዋታ ሳምንት እሰከ 90ኛዉ ደቂቃ ድረስ በሀድያ ሆሳዕና ሁለት ለዜሮ ሲየራ ቆይቶ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ባሴቆጠሯቸዉ ግቦች ሁለት አቻ መለያየት ችለዉ የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ለመዲናዉ ክለብ እጅ ለመስጠት ተገደዋል።

ዉጤቱን ተከትሎም የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ በጊዜያዊነት በ18 ነጥቦች አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፤ በተቃራኒው በምሽቱ ጨዋታ ሽንፈትን ያስተናገደዉ ሀዋሳ ከተማ በ14 ነጥቅ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በቀጣይም በ10ኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ግብር ሀዋሳ ከተማ ከጠንካራዉ ኢትዮጵያ መድን ጋር ሲገናኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ከወላይታ ዲቻ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...