……በርኖስ ማስታወቂያና ኢንተርቴይመንት እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ ይመሩታል…..
በርኖስ ማስታወቂያና ኢንተርቴይመንት እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለቀጣዮቹ 3 አመታት የሚቆይ በጋራ አብሮ የመስራት ስምምነት በይፋ ተፈራረሙ።
ዛሬ በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተካሄደ የፊርማ ስምምነት መሰረት አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ከየካቲት 8-10/2016 ድረስ በተከታታይ ሶስት ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደውን የስፖርት ፌስቲቫልንም በጋራ እንደሚያካሂዱ ይፋ አድርገዋል።
በሶስቱ ቀናት የስፖርት ፌስቲቫል ላይ 16ቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች፣ በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር ያሉ 36 ፌዴሬሽኖችና ማህበራት፣ በርካታና የትጥቅ አቅራቢዎችና የጂም ቤቶች የሚሳተፉ ሲሆን የፌስቲቫሉም አንዱ አላማ ተሳታፊዎችን በገንዘብ ማጠናከር በመሆኑ ምንም አይነት የመመዝገቢያ ክፍያ እንዳልከፈሉ ታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
በኢግዚቢሽን ማዕከል ቁጥር አንድ አዳራሽ ሁሉም ተሳታፊዎች ስለራሳቸው የሚያስተዋውቁበት ቁጥር ሁለት ደግም በገቢ ራሳቸውን የሚያጠናክሩበት ሽያጭ የሚያካሂዱበት እንደሚሆን በግቢው ውስጥ የህጻናት መቆያና መዝናኛዎችን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊዎችን የሚገልጽ ስራዎች የሚሰሩባቸው መሆኑን በመግለጫው ተወስቷል። ይኧኛው የመጀመሪያው የስፖርት ፌስቲቫል በተሻለ ይዘትና ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀጣይነት እንዲኖረው የሚናፈቅ ሆኖ በየአመቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ጠንካራ ዝግጅት እንደሚደረግ አዘጋጆቹ አስረድተዋል።
በዚሁ መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው የፌስቲቫሉ የገቢ ምንጮች ስፖንሰሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እንዲሁም በርኖስ ማስታወቂያና ኢንተርቴይመንት በጋራ የሚገኝ ሲሆን በሶስት ቀኑ የስፖርት ፌስቲቫል እስከ 50 ሺህ ሰው ይታደማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ተወካይ አቶ እንግዳ ወርቅ ዳንኤልና የበርኖስ ማስታወቂያና ኢንተርቴይመንት ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ብሩክታይት ላቀው በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተካሄደው የፊርማ ስምምነት ስነስርዓት ላይ በመገኘት ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት ማለትም እስከ 2019 ድረስ አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን በፊርማቸው አጽድቀውታል።