በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመራ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 40 ነጥቦችን በመሰብሰብ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ የቻለዉ መቻል አዲስ አሰልጣኝ በአንድ አመት ውል መሾሙ ታውቋል።
ከዚህ ቀደም በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ደቡብ ፖሊስን እና ወላይታ ዲቻን እንዲሁም በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት ደግሞ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ቆይታ የነበራቸዉ አሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራ የሌላኛዉ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ምትክ በመሆን መቻልን በአሰልጣኝነት መረከባቸዉ ተረጋግጧል።