በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ እየተመራ ወደ በዘንድሮዉ አመት ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደግ የቻለዉ እና በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን በዝውውር መስኮቱ ላይ ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ላይ የሚገኘዉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።
በዚህም በዘንድሮዉ አመት ለጣና ሞገዶቹ ውጤታማነት የጎላ አስተዋፅኦ የነበራቸዉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ፋአድ ፈረጃ እና ተከላካዩን ፈቱዲን ጀማል በሁለት አመት የኮንትራት ውል አዲስ አዳጊውን ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።