ዘግየት ብሎ ወደ ዝውውር ገበያዉ የገባው የምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ መቀላቀሉ ታውቋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም ለጂማ አባጂፋር እና ባህርዳር ከተማ መጫወት የቻለዉን እንዲሁም የተጠናቀቀዉን የውድድር ዘመን ደግሞ ከሊጉ በወረደዉ ክለብ በአርባምንጭ ከተማ ቤት ማሳለፍ የቻለዉን እና በአመቱም ዘጠኝ ያህል ጎሎችን ማስቆጠር የቻለዉን የፊት መስርመር ተጫዋች ተመስገን ደረሰ መሆኑም ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪም በአሰልጣኝ አስራት አባተ የሚመራዉ ድሬዳዋ ከተማ የሁለት ነባር ተጫዋቾቹን ውል ለተጨማሪ አመታት ማራዘሙ ታዉቋል። በዚህም አጥቂዉ ቻርልስ ሙሰጌ እና ሱራፌል ቀጣዩቹን ሁለት አመታት በብርቱካናማዎቹ ቤት ለመቀጠል ፊርማቸውን አኑረዋል።