በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መከላከል ተደርጎ ጋቶች ፓኖም ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ፈረሰኞቹ አሸንፈው ወተዋል ።
ሲዳማ ቡና በ19ኛው ሳምንት ሰበታ ከተማን ባሸነፉተብ ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 ሁለት ለውጦችን በማድረግ ፍሬው ሰለሞንን እና ብርሀኑ አሻሞን በይገዙ ቦጋለ እና ተመስገን በጅሮንድ ምትክ ሲያሰልፉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በሳምንቱ ከመከላከያ አቻ ሲለያዩ በነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ላይ አንድ ለውጥ ብቻ በማድረግ በአቤል ያለው ምትክ አዲስ ግደይን ጨዋታውን እንዲጀምር አድርገዋል ።
የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ቀዝቀዝ በላ እንቅስቃሴ የተጀመሰ እና ኳሰችን ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ የማይደርሱበትም ነበር ። በፈረሰኞቹ በኩል በነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በተለይም በመስመር በኩል ያለኮሩ የኳስ ፍሰቶች የበዙበት ሲሆኖ በሲዳማ ቡና በኩልም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎችን በአጋማሹ መመልከት ችለናል ።
በ8ኛው ደቂቃ ላይ ያብስራ ተስፋዬ በረጅም የደረሰውን ኳስ በሳጥን ውስጥ ሆኖ ማግኘት ቢችልም ከፊቱ ግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ኳሱን ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።በሲዳማ ቡና በኩል ደግሞ የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በ22ኛው ደቂቃ ላዬ የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ሳልሀዲን ሰይድ ከሳጥን ውጪ አክርሮ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ቻርለስ ሉክዋጎ መልሶታል ።
- ማሰታውቂያ -
የተጠበቀውን ያህል በሙከራዎች ያልታጀበው ጨዋታ በ43ኛው ደቂቃ ኳስ እና መረብ አገናኝቷል ። ሙሉአለም መስፍን በአማኑኤል ገብረሚካኤል ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን የቅጣት ምት ሄኖክ አዱኛ ወደ ግብ አሻግሮት የነበረ ሲሆን ተከላካዮቹ መሀሪ መና እና ያኩቡ መሀመድ ተዘናግተው ስህት በሰሩበት ሰዓት ጋቶች ፓኖም ኳሱን አግኝቶ ፈረሰኞቹን መሪ አድርጓል ። የመጀመሪያው አጋማሽም በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 – 0 መሪነት ተጠናቋል ።
በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው በተወሰነ መልኩ ከመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያስለመከተን ነበር ። ምንም እንኳን ወደ ፊች የሚሄዱ ኳሶች በርከት ቢሉም የግብ ሙከራዎች ማድረግ ለሁለቱም ቡድኖች ቀላል አልነበረም ።
በአጋማሹ የመጀመሪያ የነበረው ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በ65ኛው ደቂቃ ላይ የታየ ሲሆን ፍሬው ሰለሞን ከርቀት ላይ የተገኘውን የቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ በቻርለስ ሉክዋጎ ተመልሶበት ወጥቷል ።
ከሁለት ደቂቃዎች በኋላም ጨዋታውን በመምራት ላይ የነበሩት ፈረሰኞቹ ከቆመ ኳስ ያገኙትን የግብ አጋጣሚ ለጥቂት ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ።በ76ኛው ደቂቃ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምበል የሆነው ሀይደር ሸረፋ ተቀይሮ በመውጣት ላይ ሳለ ጊዜ በማባከኑ የመጀመሪያ የቢጫ ካርድ ሲመለከት ዳኛው የማስጠንቀቂያ ካርዱን በሰጡት ጊዜ ባሳየው ባህሪ ምክንያት በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይም በተለይም ሲዳማ ቡናዎች ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታውን በሽንፈት አጠናቀዋል ።
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 44 በማድረስ መሪነቱን ሲያጠናክር ሲዳማ ቡና ደግሞ በ33 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።በ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ቅዳሜ ቀን 9 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን ሲገጥም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታል ።