By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን ሲረከብ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ንግድ ባንክሲዳማ ቡናፋሲል ከነማ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን ሲረከብ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ በአስራ አራተኛዉ ሳምንት መርሐግብር ከወላይታ ዲቻ ጋር አንድ አቻ ተለያይቶ የነበረዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን በተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ ብቸኛ ግብ 1ለ0 በሆነ ዉጤት አሸንፏል።

በሁለቱ ክለቦች ተመጣጣኝ የሚባል የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ መካሄድ በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ገና በመባቻዉ ሙከራ ተደርጎበታል ። በዚህም በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ ብርሃኑ በቀለ ከቀኝ መስመር በኩል ወደ ግብ ክልል የላካት ኳስ የግቡን አናት ገጭታ ስትወጣ በተመሳሳይ ይሄዉ ተጫዋች በ15ተኛዉ ደቂቃ ወደ ሳጥን የላካትን ኳስ ጊት ጋት ኩት ወደ ወደ ግብ ሞክሮ ኳሷ ለጥቂት ወጥታለች። በመጀመሪያው አጋማሽ ምንም እንኳን በጨዋታ ረገድ የተሻሉ የነበሩ ቢሆኑም ነገር ግን ኢላማዉን የጠበቀ ሙከራ ለማድረግ ተቸግረዉ የነበሩት ፈረሰኞቹ በመሐል በአጥቂዉ ሞሰስ ኦዶ አማካኝነት ካደረጉት ተጠቃሽ ሙከራ ውጭ ዕድል መፍጠር ሳይችሉ የመጀመሪያዉ አጋማሽ ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ የማጥቃት ሀይላቸውን አጠናክረዉ የቀጠሉት ፈረሰኞቹ በ53ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል ሄኖክ አዱኛ ያሻገረዉን ኳስ አማኑኤል ተርፉ በግንባር ገጭቶ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ የአቻነት ግብ ለማስቆጠር በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ በማስገባት አንዳች ነገር ለመፍጠር ሲጥሩ የነበሩት ሲዳማዎች በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ዉጥናቸዉ ሰምሮ የአቻነት ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ሲቀሩ ፤ በተቃራኒው ፈረሰኞቹ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ተደጋጋሚ የሚባሉ ሙከራዎች በዳግማዊ አርአያ እና አማኑኤል ተርፉ አማካኝነት ሙከራ ማድረግ ቢችሉም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸናፊ ሆኗል።

- ማሰታውቂያ -

በዕለቱ ተጠባቂ መርሐግብር የአሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ ቡድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 4ለ2 በሆነ ዉጤት አሸንፏል !!

አመሻሽ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ በተጀመረዉ እና ማራኪ እንቅስቃሴ በተስተዋለበት የዕለቱ ጨዋታም የዳኛዉ ፊሽካ በተነፋ ገና በ10ኛዉ ደቂቃ አፄዎቹ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። በዚህም ከኋላ መስመር የተሻገረለትን ኳስ አጥቂዉ ጌታነህ ከበደ ለአማኑኤል ገ/ሚካኤል አቀብሎት አማኑኤልም ግብ ጠባቂዉን አታሎ በማለፍ ድንቅ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ገና በጨዋታዉ መባቻ ላይ ግብ ካስተናገዱ በኋላ የአቻነት ግብ በማስቆጠር ምላሽ ለመስጠት መታተር የጀመሩት ባንኮች በ27ተኛዉ ደቂቃ ላይ የአቻነት ግብ አጊኝተዋል ፤ በዚህም የፊት መስመር ተጫዋቹ አዲስ ግደይ ኳስ በእጅ በመነካቱ የተሰጠዉን ቅጣት ምት ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። የአቻነት ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ ወደ ጨዋታዉ ለመመለስ በተደጋጋሚ ጫናዎችን መፍጠር የጀመሩት አፄዎቹ ከአንድ ሁለት ተጠቃሽ ሙከራዎች በኋላ በ38ተኛዉ ደቂቃ ላይ ወሳኝ ግብ ማግኘት ችለዋል ፤ በዚህም ዮናታን ፍስሀ ከቀኝ መስመር በኩል ያሻማውን ኳስ አጥቂዉ ሽመክት ጉግሳ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን በድጋሚ መሪ ማድረግ ችሏል። በማራኪ እና ድንቅ እንቅስቃሴ የቀጠለዉ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታም የመጀመሪያው አጋማሽ ሊገባደድ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ዳግም የአቻነት ግብ አስቆጥረዋል ። በዚህም ከቅጣት ምት ኤፍሬም ታምራት ያሻገረዉን ኳስ ካሌብ ወደ ግብነት ቀይሮ አጋማሹ ሁለት አቻ ተገባዷል ።

ከዕረፍት መልስ የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ በጨዋታው ላይ ብልጫ ለመዉሰድ መጣር የጀመሩት ባንኮች በ55ተኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም በጨዋታዉ መሐል በተደጋጋሚ ስህተቶችን ሲፈፅም የነበረዉ የአፄዎቹ የግብ ዘብ ይድነቃቸው ኪዳኔ በስህተት ለኪቲካ ያቀበለዉን ኳስ ኪቲካ ለቢኒያም አቀብሎት ተጫዋቹም ወደ ግብነት ቀይሮ መሪ መሆን ችለዋል ።

የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር በማጥቃቱ ረገድ እየተዳከሙ የቀጠሉት አፄዎቹ በ79ነኛዉ ደቂቃ ላይ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ፤ በዚህም ተቀይሮ የገባዉ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ከጌታነህ ከበደ የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም የግቡ ቋሚ ኳሷን መልሷታል።

በተቃራኒው የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር ይበልጥኑ ወደ ራሳቸዉ የግብ ክልል አፈግፍገው በመጫወት አልፎ አልፎ የሚገኙ እድሎችን ለመጠቀም ይጥሩ የነበሩት ባንኮች በጭማሪ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ በገባዉ ወጣቱ ተጫዋች ዳዊት ዮሐንስ አማካኝነት ተጨማሪ ግብ አክለዉ ጨዋታው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ቡናማዎቹ ከተከታታይ ሶስት ጨዋታ በኋላ አቻ ሲወጡ ፤ ኢትዮጵያ መድን አሁንም ባለማሸነፍ ጉዞዉ ቀጥሏል !!
Next Article ባህርዳር ከተማ እና መቻል በተመሳሳይ ተጋጣሚዎቻቸዉን 1ለ0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዘዋል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ካፍዜናዎች

ካፍ ለአባል ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የሚያከፋፍለውን ዓመታዊ የገንዘብ ድጋፍ አሳደገ

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 1 year ago
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 20ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
የጨዋታ ዘገባ | የአዲስ አበባ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
”በ2014 የዉድድር አመት የተሻለውን ታፈሰ ሰርካ ጠብቁ”
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 11ኛ ሳምንት በቀጥታ / Live Score/
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?