By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: አፄዎቹ ከሲዳማ ቡና ጋር አቻ ሲለያዩ ፤ ወላይታ ዲቻም ከኢትዮጵያ መድን ጋር በተመሳሳይ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !!
Share
Notification Show More
Latest News
በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ
ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች መቐለ 70 እንደርታ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችሲዳማ ቡናየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህንፋሲል ከነማ

አፄዎቹ ከሲዳማ ቡና ጋር አቻ ሲለያዩ ፤ ወላይታ ዲቻም ከኢትዮጵያ መድን ጋር በተመሳሳይ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

ቀን 10:00 ሰዓት ሲል በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ ፊሽካ በጀመረዉ እና በእንቅስቃሴ ረገድ ቀዝቃዛ በነበረዉ የዕለቱ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ አፄዎቹ በኳስ ቁጥጥር ተሽለዉ ሲንቀሳቀሱ ፤ በተቃራኒው ሲዳማዎች ደግብ በአብዛኛው ወደ መስመር በሚላኩ ረዣዥም ኳሶች አደጋ ለመፍጠር ሲጥሩ ተስተዉሏል። በዚህ ሂደት በቀጠዉ ጨዋታም ሲዳማዎች በና በ12ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ፤ በዚህም ይገዙ ከበዛብህ የተሻገረለትን ኳስ ይገዙ ቦጋለ እየገፋ ወደ ሳጥኑ ጠርዝ ከደረሰ በኋላ ኳሷን አክርሮ ወደ ግብ ልኳት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወደ ዉጭ ወጥታለች።

ቃልኪዳን በቀኝ መስመር በኩል ከአቤል እንዳለ በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኛትን ኳስ ሳጥን ዉስጥ ደርሶ በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክርም ኳሷ ወደ ዉጭ ወጥታለች ። በተጨማሪም በአማካዩ ጋቶች ፓኖም እና ቃልኪዳን ዘላለም አማካኝነት ሌሎች እድሎችን መፍጠር የቻሉት አፄዎቹ አጋማሹ ሊገባደድ በጣት የሚቆጠሩ ደቂቃዎች በቀሩበት ወቅት ግን ግብ ተቆጥሮባቸዋል ። በዚህም በ44ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከእዮብ የተቀበለዉን ኳስ የግብ ዘቡ ይድነቃቸው መቆጣጠር አለመቻሉን ተከትሎ አጠገቡ የነበረዉ ማክል ኪፕሮል ኳሷን ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ከግቧ መቆጠር ከሁለት ደቂቃ በኋላ ግን ፋሲሎች ወዲያዉኑ የአቻነት ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም ቃልኪዳን ዘላለም ከአቤል እንዳለ የተሻገረለትን የአየር ላይ ኳስ ከተቆጣጠረ በኋላ በፍጥነት ኳሷን በሚገርም ሁኔታ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ ወደ ግብነት በመቀየር አጋማሹ ሳይጠናቀቅ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።

- ማሰታውቂያ -

ከዕረፍት መልስ በእንቅስቃሴ ረገድ ይበልጥኑ ተሽለዉ የተመለሱት አፄዎቹ በ48ተኛዉ ደቂቃ ድንቅ የግብ ዕድል መፍጠር ችለዉ ነበር ፤ በዚህም አጥቂዉ ጌታነህ ከኤልያስ ማሞ የተቀበለዉን ኳስ ወደ ግብ ቢሞክርም ግብ ጠባቂዉ መክብብ ኳሷን ይዟታል። በድጋሚ በ62ተኛዉ ደቂቃ ላይ ቃልኪዳን ዘላለም ከአቤል የተቀበለዉን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ኳሷ ስትወጣ ፤ ሲዳማ ቡናዎችም በይገዙ ቦጋለ እና በጋናዊዉ አጥቂ አማካኝነት ሁለት ድንቅ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ ነበር ።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ በ64ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከቀኝ በኩል የተገኘዉን ቅጣት ምት ተከላካዩ አምሳሉ ጥላሁን በቀጥታ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም ፤ ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ግን ሲዳማዎች የአቻነት ግብ አግኝተዋል በዚህም አጥቂዉ ማይክል ኪፕሩል ከቀኝ ጠርዝ በቀጥታ ወደ ግብ የላካት ኳስ ወደ ግብነት ተቀይራ የሁለቱ ክለቦች የቀኑ መርሐግብር ሁለት አቻ በሆነ ዉጤት ፍፃሜዉን አጊኝቷል።

* በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ መድንን ሁለት ለአንድ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል ።

ያን ያህል ተጠቃሽ ሙከራ ባልተመለከትንበት እና ደብዛዛ በነበረዉ የምሽቱ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ወላይታ ዲቻዎች በአንፃራዊነት የጨዋታ ብልጫ ወስደዉ ረዣዥም ኳሶችን ወደ ፊት መስመር በመላክ እና በፈጣን ሽግግር እድሎችን ለመፍጠር ሲጥሩ ፤ በተቃራኒው መድኖች ደግሞ በአንድ ሁለት የጨዋታ ቅብብል ወደ ሳጥን ከደረሱ በኋላ እድሎችን ፈጥረዉ ግብ ለማስቆጠር ሲንቀሳቀሱ የተስተዋሉት መድኖች ገና በመባቻዉ አቡበከር ሳኒ ያሻገራትን ኳስ ተከላካዩ አንተነህ ሲጨርፋት ያገኛት አብዲሳ ጀማል ወደ ግብ ሞክሯት ለጥቂት ወጥታለች።

ከዚች ሙከራ በኋላ እምብዛም ለዕይታ ማራኪ ባልነበረዉ የመጀመሪያዉ አጋማሽ በ34ተኛዉ ደቂቃ ላይ አብዲሳ ጀማል ናትናኤል ናሲሩ ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል። ከዕረፍት መልስ በተመሳሳይ የጨዋታ እንቅስቃሴ በቀጠለዉ የምሽቱ መርሐግብር በ54ተኛዉ ደቂቃ ላይ የጦና ንቦቹ መሪ መሆን የቻሉበትን ግቦች አግኝተዋል። በዚህም የመድን ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ ብስራት በቀለ ያገኛትን ኳስ የግብ ዘቡን አቡበከር ኑራ በማለፍ ድንቅ ጎል አስቆጥሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ ያስገቡት መድኖች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ ተሳክቶላቸው የአቻነት ግብ አግኝተዋል። በዚህም በ72ተኛዉ ደቂቃ ላይ እዮብ ተስፋየ ብሩክ ሙሉጌታ ላይ የሰራዉን ስህተት ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት አሚር ሙደሲር አስቆጥሮ ጨዋታዉን አቻ ማድረግ ችሏል።

የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር ግለቱ በተፋፋመዉ ጨዋታ በ81ኛዉ ደቂቃ ላይ ዲቻዎች ዳግም መሪ መሆን ችለዋል ፤ በዚህም ከዘላለም ኢሳያስ የተቀበለዉን ኳስ ብስራት በቀለ ወደ ግብነት ቀይሮ መድን ሁለት ለአንድ መምራት ሲጀምር ፤ ጨዋታዉ ተጠናቀቀ ተብሎ የዳኛዉ ፊሽካ ሲጠበቅ ግን መሐመድ አበራ የአቻነት ገብ አስቆጥሮ ጨዋታዉ 2ለ2 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል

You Might Also Like

በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ቅዱስ ጊዮርጊስ በአማኑኤል ኤርቦ ሁለት ጎሎች ታግዞ ጨዋታውን ሲያሸንፍ ፤ ወልቂጤ እና ሀድያም አቻ ተለያይተዋል !!
Next Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችድሬዳዋ ከተማባህርዳር ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል !!

Ermias Misganaw By Ermias Misganaw 3 years ago
የጨዋታ ዘገባ | የሁለተኛው ዙር ቀዳሚ ጨዋታ በመቻል አሸናፊነት ተጠናቋል
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ሲቀናው አዳማና ፋሲል ከነማ ነጥብ ጥለዋል
የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት ብሄራዊ ቡድን የኡጋንዳ ኣቻውን ኣሸነፈ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?