By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ሲጥል ፤ ቡናማዎቹም በአሰልጣኝ ነፃነት ስር የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ሀዲያ ሆሳዕናየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችድሬዳዋ ከተማኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ሲጥል ፤ ቡናማዎቹም በአሰልጣኝ ነፃነት ስር የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

ቀን 10:00 ሰዓት ሲል በዋና ዳኛ ማኑኄ ወልደፃዲቅ ፊሽካ በጀመረዉ እና ሁለቱም ቡድኖች ቶሎ ቶሎ ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል በመድረሱ ረገድ ድንቅ ሆነዉ በጀመሩት ጨዋታ ገና በመባቻዉ በ8ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሀድያዎች ሙከራ ማድረግ ችለዋል ፤ በዚህም ተመስገን ብርሐኑ ከብሩክ ማርቆስ የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ፍሬዉ ኳሷን ተቆጣጥሯታል። በድጋሚ ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቻሉት ሀድያዎች በ17ተኛዉ ደቂቃ ላይ በአጥቂዉ ዳዋ ሁቴሳ አማካኝነት ከርቀት ድንቅ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም ነገር ግን የግብ ዘቡ ዳግም ኳሷን አምክኗል።

በተቃራኒው በሙከራ ረገድ የተቀዛቀዘ የጨዋታ ጊዜ እያሳለፉ የቀጠሉት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የመጀመሪያው አጋማሽ ሊገባደድ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት አጥቂዉ ቢኒያም ጌታቸዉ በ41ኛዉ ደቂቃ ላይ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ሲችሉ ፤ በድጋሚ በ45ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሱለይማን ጥሩ የግብ ዕድል መፍጠር ቢችልም ግብ ሳይቆጠር አጋማሹ ተጠናቋል ።

ከዕረፍት መልስ በጨዋታ እንቅስቃሴ ረገድ ይበልጥኑ ተሻሽለዉ የተመለሱት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በ51ኛዉ ደቂቃ ላይ በቢኒያም ጌታቸዉ አማካኝነት ጥሩ ሙከራ ማድረግ ችለዉ ነበር ፤ በዚህም ተጫዋቹ ከግራ መስመር በኩል ከአዲስ ግደይ የተሻገረለትን ኳስ በፎርቢች ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ፔፔ አልዛየር ኳስን ይዞበታል። ከዚህ ተጠቃሽ የባንኮች ሙከራ ውጭ የጠራ ሙከራ ለማድረግ የተቸገሩት ሁለቱም ክቦች በሁለተኛዉ አጋማሽ ይህ ነዉ የሚባል አደጋ መፍጠር ሳይችሉ መርሐግብሩ 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት ተጠናቋል።

- ማሰታውቂያ -

– በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ መሪነት ምሽት አንድ ሰዓት ሲል በጀመረዉ የምሽቱ መርሐግብር ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2ለ1 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል ።

ተመጣጣኝ በሚባል የጨዋታ ፉክክር በጀመረዉ የምሽቱ ጨዋታ ገና በመባቻዉ ድሬዎች ከማዕዘን በተገኘ ኳስ ግብ ለማስቆጠር ተቃርበዉ የነበረ ቢሆንም ከብዙ ንክኪዎች በኋላ ተከላካዩ ወንድሜነህ ደረጀ ኳሷን አውጥቷታል። በዚህ ሂደት ጨዋታቸዉን የጀመሩት ድሬዎች በድጋሚ በ8ተኛዉ ደቂቃ ላይ ድንቅ የግብ ሙከራ ከሳጥን ውጭ አድርገው የነበረ ቢሆንም ኳሷ ግብ ጠባቂዉ በረከት በቀላሉ ተቆጣጥሮታል።

በንፅፅር በሙከራ ረገድ የተቀዛቀዙ ቢሆንም በጨዋታ እንቅስቃሴ ግን ብልጫ የነበራቸው ቡናማዎቹ በ31ኛዉ ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ኢላማዉን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ፤ በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል ሱራፌል ጌታቸዉ ያቀበለዉን ኳስ ዘርዓይ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ለጥቂት ወጥታለች። በድጋሚ በ40ኛዉ ደቂቃ ላይ ከተመሳሳይ ቦታ አብዱልከሪም ወደ ግብ ክልሉ ድንቅ ኳስ አሻምቶ የነበረ ቢሆንም መስፍን ታፈሰ በአስገራሚ ሁኔታ ሳይጠቀምባት ቀርቷል።

ከዕረፍት መልስ ፉክክር ጨምሮ በቀጠለዉ ጨዋታም በ49ነኛዉ ደቂቃ ላይ ድሬዳዋ ከተማዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል ፤ በዚህም መሐመድ አብዱለጢፍ ያሻገረለትን ኳስ ቻርልስ ሙሰጌ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል ። በዚህ ሂደት በቀጠለው ጨዋታም በ ደቂቃ ላይ ቡናማዎቹ የድሬዳዋ ከተማን ተከላካዮች አለመናበብ ተከትሎ የተፈጠረዉን ስህተት አንተነህ ተፈራ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።

የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር ተጋግሎ በቀጠለዉ ጨዋታም በ84ተኛዉ ደቂቃ ላይ ድሬዳዋ ከተማዎች ግብ አስቆጥረዉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ጥፋት መሰራቱን ተከትሎ ጎሉ ቢሻርም መደበኛዉ 90 ደቂቃ ተጠናቆ በተጨማሪ ደቂቃ ድሬዎች የማሸነፊያ ግብ አግኝተዋል ፤ በዚህም በግራ መስመር በኩል መሐመድ አብዱለጢፍ ወደ ግብ የላከዉን ኳስ ግብ ጠባቂዉ በረከት መቆጣጠር አለመቻሉን ተከትሎ ቻርልስ ሙሰጌ ሁለተኛ ግን አስቆጥሮ ክለቡን ድሬዳዋ ከተማ 2ለ1 አሸናፊ ማድረግ ችሏል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article አፄዎቹ ኢትዮጵያ መድንን ሲያሸንፉ ፤ ፈረሰኞቹም ሀምበሪቾ ዱራሜ ላይ ወሳኝ ድል ተቀዳጅተዋል !!
Next Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሰባተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግLIVESCORE

የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ /LIVESCORE/ይከታተሉ

hatricksport team By hatricksport team 8 years ago
የስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዓበይት ጉዳዮች።
የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ወንዶ ገነት አሊ ሀብቴ ጋራዥን የጋምቤላው ኑዌር ዞን አሳይታ ወረዳን ከፍፁም የጨዋታ ብልጫ ጋር አሸንፈዋል።
የጨዋታ ዘገባ | የይገዙ ቦጋለ ብቸኛ ግብ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን እንዲያስመዘግብ አድርጓል
ኢትዮጵያ በዛሬው የቻን አፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በሁለት ኢትዮጵያውያን ትወከላለች
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?