በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ የተለያዩ አዳዲስ ወጣቶችን እንዲሁም አንጋፋ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት ጅማዎች አሁን ደግሞ አንጋፋዉን አጥቂ ሰልሀዲን ሰኢድን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸዉ ታዉቋል።
በክለብ ደረጃ ከዚህ ቀደም ለሙገር ሲሚንቶ፤ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ዋዲ ዳግላ፤ሊርስ፤አል አህሊ እና ኤምሲ አልጀርስ መጫዎት የቻለዉ አጥቂዉ ረዘም ላሉ አመታት ከተጫወተበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመልቀቅ በዛሬዉ ዕለት ለጅማ አባጅፋር ፊርማዉን ማኖሩ ተረጋግጧል።
በተያያዘም ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ ዘንድሮ በዝዉዉሩ ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ጅማዎች ከዚህ ቀደም መስዑድ መሀመድን ዳዊት እስጢፋኖስን የመሳሰሉ አንጋፋ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወቃል።