ሀዋሳ ከተማ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ዉጤት ወላይታ ዲቻን 3-1 በማሸነፍ አስመዝግቧል !!
ጨዋታው ገና ከጅምሩ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉበት ሲሆን ወላይታ ዲቻዎች በጨዋታው መጀመሪያ አከባቢ በአበባየሁ አጂሶ ለጎል የቀረበ ሙከራ ማድረግ ሲችል ሀዋሳ ከነማዎች በበኩላቸዉ በበረከት ሳሙኤል ለጎል የቀረበች የሞከሯት ኳስ ተጠቃሽ ናት።
ሀዋሳ ከነማዎች ከእዛ በኋላ ደጋግመው ወደ ወላይታ ዲቻ የግብ ክልል በማምራት ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ የቻሉ ሲሆን ሙጂብ ቃሲም በ26ኛዉ ደቂቃ በግንባሩ ገጭቶ ባስቆጠራት ጎል ሀዋሳዎች 1-0 በሆነ ዉጤት መሪ መሆን ችለዋል።
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታው 1-0 በሆነ ዉጤት እስከመጀመሪያዉ አጋማሽ መጠናቀቂያ ድረስ ቢቀጥልም ቃልኪዳን ዘላለም ለወላይታ ዲቻዎች በ42ኛዉ ደቂቃ ኳሷን ከመረቡ አገናኝቶ ጨዋታዉ ወደ 1-1 ያመራ ቢሆንም ሀዋሳ ከነማዎች በሙጂብ ቃሲም በኩል በ45ኛዉ ደቂቃ ባስቆጠሯት ሁለተኛ ጎል የመጀመሪያው አጋማሽ 2-1 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።
በሁለተኛዉ አጋማሽ ሀዋሳ ከነማዎች ጥንቃቄ የታከለበት አጨዋወት ሲከተሉ የነበረ ሲሆን ወላይታ ዲቻዎች በበኩላቸው ፈጠን ባለ እንቅስቃሴ ወደ ሀዋሳ ከነማ የግብ ክልል ለመድረስ ደጋግመዉ ሲሞክሩ ነበር።
ወላይታ ዲቻዎች አዲሱን እና እዮብን ወደ ሜዳ ቀይረዉ ያስገቡ ሲሆን ጨዋታው ከመጀመሪያው ይልቅ ወደ መገባደጃዉ አከባቢ መነቃቃት ተፈጥሮበታል።
ጨዋታዉ መጀመሪያ ከነበረበት የ2-1 የጎል ልዩነት ተጨማሪ ጎል ሳይታከልበት እስከ 82ኛዉ ደቂቃ ድረስ ማምራት ቢችልም ዓሊ ሱለይማን ለሀዋሳ ከነማዎች ሶስተኛዋን ጎል አስቆጥሮ የእለቱ ጨዋታ 3-1 በሆነ በሀዋሳ ከነማ አሸናፊነት ተጠናቋል።